Call

የአማራ  ልማት ማህበር (አልማ) የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክር ቤት አባል ለመሆን ለምትፈልጉ በጎ ፈቃደኞች የቀረበ ጥሪ

የአማራ ልማት ማህበር/አልማ/ የክልሉን  ህዝብ  የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በተገቢው ሁኔታ ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት በአማራ ክልል፣ በሀገር ውስጥ ከክልሉ ውጪ እና ከሀገር ውጪ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኛ ምሁራንን በየተሰማሩበት የሞያ መስክ የበኩላቸውን አስተዋፅዎ በማበርከት እና ሳይንሳዊ በሆነ አስተሳሰብ እና አሰራር በመታገዝ አመርቂ ውጤትን ማስመዝገብ እንዲቻል ከ45-60 አባላት ያለው የአማካሪ ምክር ቤት ማቋቋም አስፈልጓል፡፡ አማካሪ ምክር ቤቱ ማህበሩ የሚሰራቸውን የትምህርት፣የጤናና ወጣቶች ስራ አድል ማስፋት የልማት ፕሮግራሞቹን በስኬታማ መንገድ እንዲመራ የመምከርና በአሰራር ሂደት የሚከሰት ችግር ሲኖር ከችግሩ የሚወጣበትን ስልት የሚያመላክት እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ  "ኑ አብረን የክልላችን የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት በጋራ እናረጋግጥ" የሚል የልማት ጥሪ ለበጎ ፈቃደኞች ያቀርባል፡፡                                                                                                                             

1.    የማህበረሰብ ልማት ምክር ቤቱ አጠቃላይ ዓላማ

የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክር ቤቱ ዋና ዓላማ ማህበሩ በሚነድፋቸው የልማትና የዕድገት ፕሮጀክቶችና ጥናቶች ላይ ለአልማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

2.   የማህበረሰብ ልማት ምክር ቤቱ ዝርዝር ዓላማዎች

2.1   በሀብት ማመንጨት ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ እና የምክር አገልግሎት መስጠት

2.2   በሰብአዊ ሀብት ልማት /ትምህርት፣ጤና እና ስራእድል ፈጠራ/ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት

2.3   ባለሀብቶች፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰለፉ የሚያስችል ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት

2.4   የባህል ፣ ታሪክ ፣ ቅርስና አካባቢ ጥበቃ ስራዎች እንዲስፋፉ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት

3.   የማህበረሰብ ልማት ምክር ቤቱ ዋና ዋና  ተግባራት

የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክርቤቱ ዋና ዓላማውን ለማስፈፀም ይችል ዘንድ የሚከተሉት ዝርዝር ተግባራት ይኖሩታል፡፡

 1. በስራ አመራር እና ማኔጅመንት ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 2. በሀብት ማመንጨት ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 3. የአባላት ልማት አሰራርና አደረጃጀት ዘመናዊ እንዲሆን ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 4. በትምህርትና ስልጠና ልማት ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 5. በጤና ልማት ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 6. በስራ እድል ፈጠራ እና የኑሮ ዘዴ ማሻሻያ ፕሮግራም ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 7. የህዝብ ግንኙነትና አስተምህሮ ስራ ዘመናዊ እንዲሆን ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 8. በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ስርዓት ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 9. በትብብር የመስራትን አሰራርና አደረጃጀት/Partnership building/ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 10. መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለማህበረሰብ ልማት አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 11. ባለሐብቶች፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች በክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 12. ህብረተሰብ አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እንዲስፋፉ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 13. ባህል፣ ታሪክና ቅርስ ለማህበረሰብ ልማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 14. በቴክኖሎጅና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 15.  ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካላትን ለማሳተፍ ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት ወዘተ ናቸው፡፡

4.   የማህበረሰብ ልማት ምክርቤት አባልነት ዝርዝር መመልመያ መስፈርት

የአልማ የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክር ቤት አባል ለመሆን በሙያው የላቀ እውቀት እና  በጎፈቃደኝነት መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው የሚከተለውን ዝርዝር መስፈርት የሚያሟላ በበጎ ፈቃደኝነት የማህበረሰብ ልማት ምክር ቤቱ እጩ አባል ሆኖ በመመዝገብ ይወዳደራል፡፡

ሀ/ በግለሰብ ደረጃ መመልመያ መስፈርቶች

 1. በሙያው 2ኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያለው
 2. ለማማከር በሚፈልግበት ሙያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ያገኘ፣
 3. 10 ዓመትና ከዛ በላይ የስራ ልምድ ያለው ፣
 4. የጥናትና ምርምር ስራዎችን የሰራ ፣
 5. በሙያው ቢያንስ ሶስት ለህትመት የበቁ ወይም ለህትመት የተዘጋጁ ስራወች ያሉት፣
 6. በሰራቸው የምርምር  ስራወች ቢያንስ ሶስት ደምበኞች ምስክርነት የሰጡትና መስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣
 7. ቢያንስ ሶስት ስልጠና ርዕሶችን የሰጠ እና ማረጋገጫማቅረብ የሚችል ፣
 8. በስነምግባሩ የተመሰገነ እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው 

ለ/ በድርጅት ደረጃ መመልመያ መስፈርቶች

አንድ የአገር ውስጥም ይሁን የውጭ ድርጅት አልማን የሚጠቅም የሙያ ድጋፍና ምክር አገልግሎት በበጎ ፍቃደኝነት መስጠት ሲፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟላ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡

 1. ድርጅቱ በተመዘገበበት አገር ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያለው
 2. ከሚመለከተው አካል በሙያዉ የሙያ ፍቃድ የተሰጠው፣
 3. ድርጅቱ ቢያንስ ለአምስት አመታት በሙያዉ የሰራ፣
 4. የምክር አገልግሎቱን ለመስጠት የሚችሉ በተ.ቁ 4 "ሀ" ስር የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ  ባለሙያ ያለው፡፡

 ምዝገባ የሚካሄድበት ሁኔታ

የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክርቤት አባል በመሆን በበጎ ፈቃድ የምክር አገልግሎት ለመስጠት የምትፈልጉ ከዚህ በታች በቀረቡት አድራሻዎች  እስከ ጥር 15/2012 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የኢማል አድራሻ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በአካል በመገኘት ለመመዝገብ  አማራ ልማት ማህበር/አልማ / ዋናው መ/ቤት(ባህርዳር) ቢሮ ቁጥር 415 ወይንም 301

ምስራቅ ጎጃም አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ደብረማርቆስ ስ.ቁ +251587717056)

ምእራብ ጎጃምና አካባባው አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ( ባህርዳር ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር+251582201088)

ጎንደርና አካባቢ  አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ጎንደር ስ.ቁ +251581114649)

ደቡብ ጎንደር አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ደብረታቦር ስ.ቁ +251584410148)

ሰሜን ወሎና አካባባው  አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ወልዲያ ስ.ቁ +251333311790)

ደቡብ ወሎና አከላባባው አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ደሴ ስ.ቁ +251331117247)

ሰሜን ሸዋ  አልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ደብረብርሀን ስ.ቁ +251116816974)

አዲስ አበባ አልማ  ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (አዲስ አበባ ቦሌ ማተሚያ ቤት ጎን )(አ/አ ስ.ቁ. +251115517795)

በፖስታ በመላክ ለምትፈልጉ የፓስታ ሳጥን ቁጥር ባ/ዳር 307 እንዲሁም አ/አበባ 13685 መሆኑን እንደልፃለን፡፡

 

 

የአማራ  ልማት ማህበር (አልማ) የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክር ቤት በጎ ፈቃደኛ አባል ለመሆን የማመልከቻ ቅፅ

 

የአመልካች ስም------------------------------------ የአባት ስም----------------------- የአያት ስም-----------------------

የትምህርት ደረጃ -----------------------------

የሰለጠኑበት ሞያ ዘርፍ------------------------

አማካሪ ምክር ቤቱን ለማገልገል የሚፈልጉበት የሞያ ዘርፍ ---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የመኖሪያ አድራሻ------------------------------

ስልክ ቁጥር---------------------

የኢማል አድራሻ ------------------

እኔ ------------------------------------------------- የተባልኩ የአማራ  ልማት ማህበር (አልማ) የማህበረሰብ ልማት አማካሪ ምክር ቤት የበጎ ፈቃደኛ አባል በመሆን ባለኝ እውቀት እና ሞያ የበኩሌን ድረሻ ለማበርከት ሙሉ ፈቃደኛ ስለሆንኩ  ማህበሩ የአማካሪ ምክርቤቱ አባል እንድሆን እንዲፈቅድልኝ በትህትና አመለክታለሁ ፡፡

የአመልካች ሙሉ ስም ----------------------

የአመልካች ፊርማ------------------------------

ቀን -------------------------------


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede