የባ/ዳር ቀጠና አልማ ጽ/ቤት ከዕቅዳቸው 100% እና በላይ የፈጸሙ ወረዳዎችንና ከተማ አስተዳደሮችን  ሸለመ::

ባ/ዳር ቀጠና አልማ ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የማህበሩ ዕቅዳቸውን 100% እና በላይ ለፈጸሙ 6 ወረዳዎችና 3 የከተማ አስተዳደሮችን ከ130 ሽህ በላይ የሚያወጡና ለጽ/ቤቶቹ ለወደፊት ሥራቸው መሳለጥ አጋዥ የሆኑ ቁሳቁሶችን ሸለመ፡፡

በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ የባ/ዳር ቀጠና አልማ ጽ/ቤት በ2005 ዓ/ም በአባላት ማፍራት ስራና ለልማት የሚውል ሃብት በማሰባሰብ ከዕቅዳቸው 100% እና በላይ ለፈጸሙ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የሸለመው ሐምሌ 19/2005 ዓ/ም በመርዓዊ ከተማ ባካሄደው የ2005 የእቅድ አፈፃጸምና የ2006 ዓ/ም ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ ነው፡፡

ቀጠናው የባ/ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በምዕ/ጎጃም ዞን መስተዳድር ውስጥ የሚገኙ 13 ወረዳዎችንና 5 የከተማ አስተዳደሮችን ያካተተ ነው፡፡ በእነዚሁ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በተደረገው የአመታዊ ዕቅድ አፈፃጸም ቀጥለው የተዘረዘሩት ተከታዩን ደረጃና ሽልማት አግኝተዋል፡፡

ተ.ቁ  ወረዳ           ደረጃ     የሽልማት ዓይነት             
1 ሜጫ ወረዳ 1ኛ ዲል ኮምፒዩተርና ፕሪንተር
2 ይልማና ዴንሳ 2ኛ ዲል ኮምፒዩተርና የአመቱን ዋንጫ
3 ቋሪት  3ኛ ዲል ኮምፒዩተርና
4 ጃቢ ጠህናን 4ኛ ፕሪንተር
5 ቡሬ ዙሪያ 5ኛ ፕሪንተር
6 ደጋ ዳሞት 6ኛ ፕሪንተር
የከተማ አስተዳደሮች
1 መርዓዊ ከተማ 1ኛ 32 ኢንች ፋና ቴሌቪዥን
2 አዴት ከተማ 2ኛ 23 ኢንች ፋና ቴሌቪዥን
3 ፍ/ሰላም ከተማ 3ኛ 19 ኢንች ፋና ቴሌቪዥን

ከዚህም በተጨማሪ በቀጠናው ለሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለተገኘው ውጤት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምዕ/ጎጃም መስተዳድር ዞንና የምዕራብ ጎጃም ብአዴን ጽ/ቤት እያንዳንዳቸው ቶሽባ ላፕ ቶፕ ኮምፒዩተሮር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ቀጠናው በበጀት ዓመቱ አባላት በማፍራትና ለልማት የሚውል ሃብት በማሰባሰብ የዕቅዱን 120% መፈጸሙን የገለጹት  የባ/ዳር ቀጠና አልማ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስዩም መለስ ለገሰ ለዚህ ከፍተኛ ውጤት መሳካትም በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የቀጠናው ሠራተኞች እንዲሁም የቶፕ አፕ ተከፋዮች በጋራ ልማታዊ አስተሳሰብ ተግባብቶና ተናቦ የመስራት ባህልን በማዳበራቸው መሆኑን አስረድተው ለሁሉም አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ ይህም የአልማ የ5 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አተገባበር አንዱ አቅጣጫ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

በመጨረሻም የባ/ዳር ቀጠና ለወረዳዎችና ለከተማ አስተዳደሮች የማበረታቻ ሽልማት ማበርከቱ በአልማ የዞኑን የቀጣይ ዕቅድ በበለጠ ተግባራዊ ለማድረግ ተነሳሽነትንና የውድድር መንፈስን እንደሚፈጥር የምዕ/ጎጃም መስተዳድር ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ዘለቀ አንሉ ገልጸዋል::

 


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede