ቆቦ ከተማ አስተዳደር በ1.5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባው የቆቦ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት  ተመረቀ፡፡                                        

   ትምህርት ቤቱን መርቀው የከፈቱት የአልማ የአባላት ልማት ፕሮግራም  ዳይሬክተር አቶ ጌቴ ሙላትና የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በላይ አያሌው  ሲሆኑ የግንባታውን1.3 ሚሊየን ብር የተሸፈነዉ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለአልማ 2002፡ልማታዊ ህብረት ቃል በገባው መሰረት ሲሆን ቀሪው  በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር የተሸፈነ ነው፡፡
እንደገለፁት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአልማ 2002፡ ልማታዊ ህብረት የገቢ ማሰባሰቢያ ወቅት ቃል በገባው መሰረት  በ1.5 ሚሊዮን ብር ይህን የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መገንባቱ የሁለቱን ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ትስስርና መረዳዳት በተግባር ለመረጋገጡ ትልቅ ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡    
 የቆቦ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሥባጋዲሥ ኪሮሰ እንደገለፁት  ተማሪዎች  ትምህርታቸዉን ለመከታተል ረጅም መንገድ አቋርጠው ይጓዙ እንደነበር አውስተው አሁን ይህ ት/ቤት በአቅራቢያችን  መገንባቱ  የረጅም ዓመታት ጥያቄያቸዉ በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር/አልማ/ በኩል ምላሽ መሰጠቱ አስደስቶናል ብለዋል፡፡  
   በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ የአባላት ልማት ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ጌቴ ሙላት በበኩላቸው  በአልማ 2002፡ ልማታዊ ህብረት የሃብት ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የፕሮጀክቶች ዕቅድ 308 ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም የተመረቀዉን የቆቦ ከተማ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጨምሮ 172 ፕሮጀክቶች ግንባታቸዉ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል፡፡

 

የልማታዊ ህብረቱ ፍሬዎች ከሆኑትና በሰሜን ወሎ መስተዳድር ዞን ዉስጥ በዋድላ፣በመቄት፣በግዳን ወረዳዎችና በቆቦ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፤ አንዲሁም በወልድያ ከተማ አስተዳደር ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ደረጃቸዉን የጠበቁ የቤተ-ሙከራ ፣ የቤተ-መጽሐፍትና የአዳራሽ ግንባታዎች የሚጠቀሱ ናቸዉ ብለዋል፡፡

አቶ ጌቴ ሙላት አክለዉም የትምህርት ሽፋንንና አጠቃላይ የትምርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ እገዛ ያለዉና አጠቃይ ወጭዉ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነዉ ይህ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር/አልማ/ እና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትብብር ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ  ተገንብቶ ለቆቦ ከተማ ህዝብና ተማሪዎች ተገቢዉን አገልግሎት ለመስጠት በመብቃቱ ደስታ ተሰምቶኛል፤ ስለሆነም እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን አገራዊ የህዳሴ ጉዟችንን ማሳካት እንችል ዘንድ የገባነዉን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር ይህን ት/ቤት ከነሙሉ ግብዓቱ ገንብቶ ላስረከበን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባልሁ ብለዋል፡፡

    ሺህ ሆነን እንደ አንድ-አንድ ሆነን እንደ አንድ ሺ!

ለበለጠና ለላቀ የልማት ተጠቃሚነት የግንቦት 20 ፍሬ የሆነዉን አማራ አቀፍ ልማት ማህበርን እናጠናክር!


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede