ሰራተኞቹና አመራሩ የገዙትን  የብር  1 ሚሊየን 515 ሺ 922 ከ 05 ሳንቲም  ርክክብ ያደረጉት ማህበሩ እየተገበረ የሚገኘውን የለውጥ አመራር የሰራዊት ልማት ግንባታ በ 2006 በጀት ዓመት  ባስገኘው ጠቀሜታና የወደፊት አቅጣጫ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

ቦንዱን ያስረከቡት የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መሀመድ ሰይድ ይመር እንደገለፁት፤ የልማት ማህበሩ ሰራተኞችና አመራሩ የታላቁ የህዳሴ ግድብ  የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ በደመወዛቸው ቦንድ በመግዛትና እና በሞራል እያሳዩ የሚገኙት  ሁለንተናዊ  ድጋፍ  እጅግ የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በእኛው ፋይናንስና በእኛው ባለሙያ እየተገነባ የሚገኘው የሀገራችን ህዳሴ ፕሮጀክት ከ40 በመቶ በላይ መጠናቀቁ እጅግ ያስደሰታቸው መሆኑን የገለፁት የማህበሩ አመራርና ሰራተኞች  ወደፊትም  ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የማህበሩ አመራርና ሠራተኞች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቁጠባ ባህላቸውን በማዳበር ረገድ የፈጠረው አጋጣሚ ትልቅ ምዕራፍን እንደሚይዝ ገልፀዋል፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede