አማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ በ2007 ዓ.ም 1000 ት/ቤቶችን በሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ለመደገፍና ቅድመ ዝግጅት መጨረሱን ገለፀ፡፡

ልማት ማህበሩ የዴቪድና ሉስሊ ፓካርድ ፋዉንዴሽን የ2006 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጸዉ ፤በሁሉም የብሄራዊ ክልሉ መስተዳድር ዞኖች የተመጣጠነና ደረጃዉን የጠበቀ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን በመደገፍ በ2007 ዓ.ም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገዉ ርብርብ ልማት ማህበሩ የብሄራዊ ክልሉ ህዝብ ልማት ሁለኛ አጋር መሆኑን ማሳያ አድርጎ ይሰራል ብሏል፡፡

ልማት ማህበሩ ይህንኑ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ድጋፍ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ዉስጥ ወደ ሶስት ሺህ እንደሚያሳድገዉ ያስታወቀ ሲሆን፣ ለዚሁ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚዉል ብር   156   ሚሊዮን በጀት መመደቡን የማህበሩ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሃመድ ሰይድ ገልፀዋል፡፡

ሞዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ድጋፍ ከክልሉ ትምህርት ቢሮና ከተማሪ ወላጆች ጋር በጋራ እንደሚከናወን የገለፀዉ ልማት ማህበሩ የመማሪያ ክፍሎች፣ የህጻናት ተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁስና ሌሎችንም ፕሮግራሙ ወደፊት ሊመራ ስለሚችልበት ስትራቴጅክ ዕቅድ አጠናቋል፡፡

ልማት ማህበሩ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ጊዜ ዉስጥ በብሄራዊ  ክልሉ ሶስት ሺህ ምዴል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን በመደገፍ የብሄራዊ ክልሉን የትምህርት ጥራት በመደገፍ አጋርነቱን እንደሚያረጋግጥ ተገልጿል ፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede