ከ2.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስና ቁሰቀቁስ ድጋፍ  ማድረጋቸውን  በሰሜን አሜሪካ የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር/አልማ/ የቦርድ ሰብሳቢ ገለፁ፡፡

የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሀይለስላሴ ቸኮል እንደገለፁት በአማራ ክልል ከ2002 ዓ.ም በተካሄደው ልማታዊ ህብረት   ተከትሎ  በተፈጠረው ልማታዊ መነሳሳት በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና የክልሉ ልማት ደጋፌዎች 2.ሚሊዮን 339 ሽህ 985 ዶላር አሰባስበው ወደ አገር ቤት መላክ ተችሏል፡፡

ድጋፉን በዘላቂነት መቀጠል የሚያስችል በአራት ቻፕተሮች የተዋቀረ ጠንካራ አደረጃጀት መፈጠሩን የጠቀሱት አቶ ሀይለስላሴ ፤ የአባላት ማፍራቱንና ሀብት አሰባሰብ ስራው ተጠናቅሮ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ብስራት ጋሻውጠና በበኩላቸው በሰሜን አሜሪካም ሆነ በሌሎች የአውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ  የሚኖሩ  የአማራ ተወላጆችና የልማት ማህበሩ ደጋፉዎች የክልላቸውንና የአገራቸውን ህዳሴ ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ፤  አጋርነታቸውን  አድንቀው ፤ የእነዚህን ወገኖች  ሙሉ አቅም  በተደራጀ መንገድ ለመምራት የሚስችል ስትራተጅ ተነድፎ ወደ ተግባር እየተገባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede