በኢ-ግሊመር ኦፍ ሆፕ ፋውንዴሽን መስራችና ፕሬዚዳንት  ወ/ሮ ዶና በርበር የሚመራው ዓለማቀፍ ዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ቡድን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ የተከናወኑ የማህበራዊ ልማትና የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ቡድኑ በሊቦ ከምከም ወረዳ ለቀጣይ 4 አመት የሚከናወኑ ተመሳሳይ ስራዎችንም አስጀምረዋል፡፡

ዛሬ ጥዋት ባህር ዳር የገባውና 13 አባላት ያሉት የዓለማቀፍ ርዳታ ሰጭውች ቡድን በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ አማራ መልሶ መቋቋም ድርጅት/ አመልድ/ ና  በኢ-ግሊመር ኦፍ ሆፕ ፋውንዴሽን ባለፉት 10 ዓመታት በጎንደር ዙሪያ የተከናወኑ የተቀናጀ ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ  ከጎበኘ በኋላ ስኬታማ  ተግባራት ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

የኢ-ግሊመር ኦፍ ሆፕ ፋውንዴሽን መስራችና ፕሬዚዳንት የሆኑት የልዑካኑ መሪ ወ/ሮ ዶና በርበር ፋውንዴሽናቸው ከአልማና አመልድ ጋር በቅንጅት ያከናወናቸው የተቀናጀ ማህበረሰብ ልማት ስራዎች ያስደሰታቸው መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ አራት አመት በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምከም ወረዳ  በትምህርት ለጤና እና ለኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች 180 ሚሊዮን ብር ተግባራዊ እንዲሆን መፈቀዱን ገልፀዋል፡፡

ለልዖካን ቡድኑ በአልማና አመልድ በኩል የተዘጋጀ ልዩ ልዩ ስጦታ በጎንደር ጎሀ ሆቴል  የተበረከተላቸው ሲሆን ለበጎ አድራጊዎች በአማራ ክልል ህዝብና በፕሮጀክት ተጠቃሚው ህዝብ ስም በክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተፈረመበት  የምስጋናና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede