አልማ በአማራ ክልል 110 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን የዲጅታል ቤተ-መፅሀፍት ተጠቃሚ የሚያደርግ ቴክኒዮሎጅ ተከላ ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የደሴና አካባቢው አልማ ፅ/ቤት ሀላፌ አቶ አበባው ታደሰ እንደገለፁት አልማ ከሌሎች ክልሎች ከሚገኙ አባላቱና ደጋፌዎቹ በተገኘ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ  በክልሉ 110 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የዲጂታል ቤተ-መፅሀፍት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ እያከናወነ ነው፡፡

ዲጅታል ቤተ-መፅሀፍቱ በ800 ሜትር ራዲየስ እስከ 2 መቶ ሺ የመማሪያና፣ የማጣቀሻ መፃህፍትን ተማሪዎች ኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት በላብቶፕ ፤በተንቀሳቃሽ ስልክና ሌሎች ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች  መጠቀም የሚያስችል ነው እንደ አቶ አበባው ገለፃ ፡፡

 ከክልሉ ሁሉም ዞኖች በፍትሀዊነት በመተከል ላይ የሚገኘው ገመድ አልባ ዲጂታል  ቤተ-መፅሀፍት በአሁኑ ሰዓት 110 ሺ ልዩ ልዩ መፅሀፍት የተጫኑበት ሲሆን ተማሪዎች የቴክስት፤ኦዲዮና ቪዲዮዎችን  ማውረድ    የፕላዝማ ትምህርትን መጠቀም  የሚያስችል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ዲጂታል ቤተ-መፅሀፍቱ በሰሜን ወሎ ፤ኦሮሚያ፤ደቡብና ሰሜን ወሎ ፤ዋግ ህምራ የተከናወነና ተማሪዎች በመጠቀም ላ㝕 ሲሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት በቀሪዎች የአማራ ክልል ዞኖች ተከላው ይጠናቀቃ፡፡Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede