ንባብ ለኢትዮጲያ ዕድገትና ብልፅግና የማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጀክት (READ C.O)  የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አንዱ ግብዓት ሆኖ ያገለግላል ሲሉ የትምህርት አመራሮች ገለፁ፡፡

የጎንደር ማዕከላዊ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፌ አቶ መስፍን እርካቤ አልማ - READ C.O  ፕሮጀክት ባለፉት አራት አመታት በዞኑ 860 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ …ተማሪዎችን የንባብና ፅህፈት ክህሎት በማሻሻል ተጠቃሚ ልምድ ተቀስሞበታል ብለዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፌ አቶ ያዜ ሀብቴ .በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዞን ደረጃ በ245 ት/ቤቶች  የህፃናትን የማንበብና ፅህፈት ክህሎት በማሻሻል ለትምህርት ጥራት ለማምጣት ሁነኛ ግብዓት መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ የትምህርት መዋቅሩና ህብረተሰቡ ፕሮጀክቱን በማስፋትና በማስቀጠል እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የስርዓተ-ትምህርት ትግበራ ባለሙያ ወ/ሮ ሰርካለም አሰፋ   ፕሮጀክቱ ባለፉት አራት አመታት በነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት አዕምሮን በንባብና በፅህፈት ክህሎተ በመግራት ልምድ የተቀሰመበት መሆኑን ገልፃው በቀጣይ ከሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ጋር በቸክ ሊስት አካተው እንደሚያስቀጥሉት አስረድተዋል፡፡

አቶ መዝገበ አንዷለም በአልማ የፕሮግራም ማናጅመንት ም/ዳይሬክተር ፕሮጀክቱ ከጃንዋሪ 01/2016 እስከ ዲሰምበር 30/2018 በፋይናንስ ምንጩ ዩኤስ አይዲ. (USID) በቴክኒካል ድጋፍ ሰጭው ሴቭ ዘ ችልደረን (Save The Children)  በፈፃሚው አልማ ፤ በትምህርት መዋቅሩና በበጎ ፋቃደኞች የላቀ ትብብር ስኬታማ አፈፃፃም አሳይቷል፡፡ ውጤታችንም ተጨማሪ የሀብት ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በጋራ ሰርተን በጋራ ተጠቃሚነታችንን እናረጋግጣለን ያሉት አቶ መዝገበ አልማ-READ CO.I  ውጤታማ በመሆናችን በቀጣይ  ለ READ CO.II በደቡብ ወሎና፤ ሰሜን ሸዋ ዞኖች ቀጣይነቱ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ 

፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede