አገራዊ ለውጡ የህዝባችንን  ጥቅሞች በመጠበቅ ዘላቂነቱ ይረጋገጣል ሲሉ አቶ መላኩ ፋንታ ገለፁ፡፡

ህዝቡ በተለይም  ወጣቱ በከፈለው  የህይወት፤ አካልና ቁሳቁስ መስዋዕትነት የተገኘው ሀገራዊ ለውጥ የህዝቡን ጥቅሞች በማስጠበቅና በማስፋት ዘላቂነቱ ሊረጋገጥ ይገባል ሲሉ የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ ገለፁ፡፡

አቶ መላኩ ፋንታ 

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ

ዋና ስራ አስፈፃሚው ክቡር አቶ መላኩ ፋንታ የማህበሩን የአጭር ጊዜ ዕቅድ አስመልክቶ  ለሁሉም ማስተባበሪያ ፅ/ቤቶች ባስተላለፉት መልዕክት  እንደገለፁት ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት የአማራ ክልል ህዝብ የመሰረተ-ልማት አልተሟላልኝም ፤ የፍትሀዊ ሀብት ክፍፍል ችግርና በሀገሪቱ ይካሄድ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ችግር ቅሬታውን በህዝባዊ አመፅ ገልጧል፡፡ ወጣቱም ይህ ለውጥ እንዲመጣ የህይወትና አካል መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል፡፡

ህብረተሰባችንን የማህበራዊ መሰረተ-ልማቶች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ለይቶ መፈፀም በመስዋዕትነት የተገኘው ለውጥ ቀጣይነት ማረጋገጥ ነው ያሉት አቶ መላኩ  በፌታችን ሁለት አመታት በክልሉ የዳስና የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶችን ጨምሮበብሄራዊ ክልሉ  የሚገኙ  ሁሉም የትምህርት ተቋማት ደረጃቸውን የማስጠበቅ  ስራ ማህበራቸው አልማ  ለመስራት መዘጋጀቱን  ገልፀዋል፡፡

የለውጡን ዓላማዎች በመደገፍ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ የክልልና ፌደራል ሚዲያዎች፤ ፤የዳያስፖራ አባላት ፤ የወጣት አደረጃጀቶች ፤በጎ ፈቃደኞች ፤የኮርፖሬት አባላትና የክልሉ አመራር አልማ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያደረወገው ርብርብ ከጎኑ ብቻ ሳይሆን ከፌት ሆነው ለውጡን በመደገፍና በመምራት ያሳዩትን ርብርብ በልማት እንደሚደግሙት ዕምነት እንዳላቸው አቶ መላኩ ገልፀዋል፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede