በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገቡ።

በዋሽንግተን ዲሲ በተዘጋጀው የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ መቀየሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ከ 1ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ ተሰብስቧል።

የዳስ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የአማራ ተወላጅ ግለሰቦች ሦስት ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ቃል ገብተዋል፤ በዝግጅቱም በጨረታ ብቻ 51 ሺህ 260 ዶላር ወይም 1ሚሊዮን 538 ሽህ የሚደርስ ብር ተሰብስቧል።

ከአማራ ተወላጆች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር የተደረጉ ምክክሮች ስኬታማ እንደሆኑ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡

የሥራ ኃላፊዎቹ በሰሜን አሜሪካ ግዛቶች ከሕዝብ ጋር ሲያካሂዷቸው የነበሩትን ምክክሮች አስመልክተው ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ የተመራ የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በሰሜን አሜሪካ-ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው፣ አትላንታ፣ ዴንቨር፣ ኮሎምበስ፣ ሚኒሶታ፣ ሳንሆዜ እና ሲያትል ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና የአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵዉያን ጋር ሲመክር መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ ምክክሩ በክልላዊ እና ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በክልሉ ልማት እና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የአልማን የቀጣይ ሦስት ዓመታት የለውጥ ዕቅድ ዕውን ለማድረግ እና ዓላማውን በዘላቂነት ለመደገፍ የዳያስፖራው ሚና ምን መሆን እንዳለበትም በምክክሩ ትኩረት ተደርጓል፡፡ ከተሳታፊዎችም በሁሉም ዘርፎች ጥያቄ እና ምክረ ሀሳቦች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

አሰራርን በአሳታፊና ቅንጅታዊ መርህ መተግበር ህዝባዊ አመኔታ ይፈጥራል!

 አሰራርን በአሳታፊና ቅንጅታዊ መርህ መተግበር የተቋምን ዘላቂነት ብቻ ሳይሆን ማህበሩ የቆመለትን የህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስችላል ሲሉ የአማራ አቀፍ ልማት

አልማ አባላቱ ወደውና ፈቅደው ማህበራዊ ችግራቸውን የሚፈቱበት ተቋም ሊሆን እንደሚገባ የማህበሩ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የአማራን ህዝብ ብሄርተኝነትን በተደራጀ መንገድ ማጎልበትና በላቀ ህዝባዊ ተሳትፎ የማህበራዊ ልማትን ማረጋገጥ ወቅቱ የሚጠይቀው አጀንዳ መሆኑን የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር/አልማ/ ስራ አመራር ቦርድ አስታወቀ፡፡

የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢው ክቡር አቶ ተፈራ ደርበው በማህበሩን የ2011 ዓ.ም ዘጠኝ ወር አፈፃፀም የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ  እንደገለፁት አልማ በበጀት አመቱ የአባል ማፍራና የልማት ሀብት አሰባሰብ ስራው ከስትራተጅክ ዕቅዱ አንፃር ውጤታማ ቢሆንም በበጀት አመቱ የልማት ሀብትን ከግብር ነጥሎ ለመሰብሰብ ከነበርው ዕቅድ አንፃር የሚፈለገውን ያህል አላሳካም፡፡

ታላቅ የተሳትፎ ጥሪ!

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ) በበጐ አድራጐት ማህበራትና ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት በ1984 ዓ/ም የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን፣በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት በግልጽ እንደተቀመጠው የማህበሩ ዋና ዓላማ የራስን/የህዝቡን የልማት ፍላጎት በራስ አቅም እውን የማድረግ አስተሳሰብና ተግባራዊ እንቅስቃሴን ለማጎልበትና ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ማህበሩ የክልሉን ሕዝብና መንግስት የልማት እንቅስቃሴ በተደራጀ ሕዝባዊ ተሳትፎና ንቅናቄ ስርዓት ባለው መንገድ ለመደገፍ ያስችለው ዘንድ የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች አሉት፡፡ እነሱም፡-

የአልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የዳታቤዝ ሰራተኞች ዘመናዊ የዳታ ቤዝ አጠቃቀምሥልጠና ተሰጣቸው!

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች የዳታ ቤዝ ሰራተኞች ያላቸውን የዳታቤዝ ክህሎት ለማሣደግ የሚያስችል በተግባር የተደገፈ የሁለት ቀናት ሥልጠና በማህበሩ    የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት ተሰጣቸው፡፡

 የአማራ ክልልን ትምህርት ተቋማት ደረጃ የማሻሻል ስራ ተቀናጅቶ ወደ ተግባር መግባት ይጠይቃል ተባለ፡፡ 

ከ1047 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 207 ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው ሲሉ የሰሜን ጎንደር ማዕከላዊ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለፀ፡፡

መምሪያ ሀላፊው አቶ መስፍን እርካቤ  ይህን የገለፁት አልማ-ኢ-ግሊመር ኦፍ ሆፕ ፋውንዴሽን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በቀጣይ አንድ አመት የሚተገብረውን የትምህርትና ጤና ፕሮጀክት ለህብረተሰቡ በሚያስተዋውቅበት መድረክ ነው፡፡

አልማ-ኢ ግሊመር ኦፍ ሆፕ ፋውንዴሽን በአምስተኛ ምዕራፉ ለጎንደር ዙሪያ ወረዳ 19.2 ሚሊዮን ብር የልማት ሀብት መደበ፡፡

አልማ-አ-ግሊመር ኦፍ ሆፕ ፋውንዴሽን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከ2007 -2010 ቆይታው በ75 ሚሊዮን 266 ሸ ብር መድቦ 54 ሺ 416 ህዝብ የጠየና ተቋማትና አገልግሎት ፤6 ሺ 818 ተማሪዎችን የትምህርት የእንስሳት ህክምና እና በሺዎች ለሚቆጠሩ የትምህርትና ጠየና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ተጠቃሚ ማድረጉን በአልማ የፕሮግራም ማናጅመንት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ ገልፀዋል፡፡


Copyright © 2012  ADA, All Rights Reserved.               Designed & Developed by :Yibeltal Ferede