የአማራ ልማት ማህበር በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ግንባር አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የዕለት ደራሽ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ፡፡

Posted on : August: 31/21
Card image

የአማራ ልማት ማህበር በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ግንባር አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የዕለት ደራሽ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አረጋው ታደሰ እንዳሉት አልማ ህዝቡን ተሳቢ አድጎ የሚሰራ የልማት ተቋም በመሆኑ በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ለዕለት ምግብ የሚውል 220 ኩንታል ፊኖ ዱቄት በጥቃቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል ፡፡ የደረሰው ጉዳትም ከፍተኛ በመሆኑ አልማ በቀጣይ መንግሰታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶችንና ግለሰቦችን በማስተባባር ለሌሎች አካባቢዎችም ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡አልማ የክልሉ በጎ ፈቃደኞች የልማት ማህበር እንደመሆኑ መጠን በቋሚነት ከሚያደረገው ዘላቂ የማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን ሰው ሰራሽም ይሁን የተፈጥሮ አደጋ በአጋጠመ ወቅት ፈጥኖ ደራሻ መሆኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት አሳይቷል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በአለማቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ በመከላከል፡ የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ፡በአጣየና መተከል ተፈናቃዮች በሚሊዮኖች የሚገመት የቁሳቁስና ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው ትህነግ በክልሉ ዋግ ህምራ ፡ራያ ፡ወልድያና ደቡብ ጎንደር ጋይንት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ አድርጎ የዕለት ደራሽ ፊኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል። አቶ አለምነው ክንዴ የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እንዳሉት በከተማቸው አሸባሪው ትህነግ በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶችና በግለሰቦች ሃብትና ንብረት ላይ ያደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ለጋሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈው አልማ ፈጥኖ በመድረሱ የህዘብ አጋነቱን አሳይቷልና እናመሰግነዋለን ብለዋል፡፡ አቶ ታደገ አለማረው የነፋስ መውጫ ከተማ ተወላጅ እንዳሉት በከተማው የደረሰው ጉዳት ከገለጻ በላይ ነው ያሉት እናም ይህን ጊዜ የበለጠ ርስበርስ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ከተጎዶ ወገኖቻችን ጋ ጎን ልንቆም ይገባል ብለው የአልማን አርአያነት ያለው ተግባር ተከትለው ሌሎችም የድጋፍ ዕጆቻቸውን ሊዘረጉ ይገባል ብለዋል፡፡

Gallary


The News