በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ምዕመናንና ካህናት፤ ዲያናትና ሊቃውንት ኢትዮጲያ ክፉ በገጠማት ወቅት ፈጥነው የሚደርሱ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን እያስመሰከሩ መሆኑን በኢትየዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሰሜን ወሎና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሀገረ-ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ገለፁ፡፡

Posted on : February: 25/22
Card image

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ምዕመናንና ካህናት፤ ዲያናትና ሊቃውንት ኢትዮጲያ ክፉ በገጠማት ወቅት ፈጥነው የሚደርሱ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን እያስመሰከሩ መሆኑን በኢትየዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሰሜን ወሎና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሀገረ-ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ገለፁ፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ይህን የገለፁት በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሀገረ ስብከት ምዕመናን፤ ካህናትና ዲያቆናት በብፁ አቡነ ማርቆስና መልዐከ አሚን ዶ/ር ፋሲል አስረስ በኩል የላኩትን 1 ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር ወጭ የተደረገበትን 375 ኩንታል የስንዴ ዱቄት ለዞኑ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ርክክብ በተደረገበት ወቅት ላይ ነው፡፡ ብፁዕነታቸው ጨምረው እንዳብራሩት በመላው አለምም ሆነ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስተዋህዶ ሃይማኖት የዋሽንግተን፤ ኦሪገንና አይዳሆና አካባቢው ምዕመናን፤ ካህናትና ዲያቆናት ኢትዮጰያ ክብርና አንድነትን የሚፈታተኑትን የውጭም ሆነ የውስጥ ሀይሎች እጃቸውን እንዲሰበስቡ በአንድነት ድምፃቸውን በማሰማት፤ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕከለት ደራሽ ምግብና ቁሳቁስ በመላክ ተጎጅ ወገኖች ድረስ በመጓጓዝ በአካል በማፅናናት እያደረጋችሁ የምትገኙት አስተዋፅኦ በእግዚአብሄር ዘንድ በረከት የምታገኙበት እንዲሆንላችሁ ተመኝተዋል፡፡ በቀጣይ ከዕለት ደራሽ ዕርዳታ በተጨማሪ የወደሙ ትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማትን መልሶ መቋቋም ስራ ላይ ብናተኩር ውጤት እናመጣለን ብለዋል ብፁ አቡነ ኤርሚያስ፡፡ በኢትዮጲያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዋሽንግተን፣ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ወንድሞቻችሁ ሀብት አሰባስቦ ከመላክ ባለፈ የጉደቱን መጠን በቦታው ተገኝተን እንድናያችሁና እንድናፅናና በመሆኑ የጠፋውን ህይወት መመለስ ባይቻልም በቀጣይ የወደመውን ሀብታችሁንና ንብረታችሁን መልሶ ለመገንባት ከጎናችሀ የማይለዩ መሆኑን መልዕክታቸው ሊደርሳችሁ ይገባል ብለዋል ፡፡ በኢትዮጲ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልዐከ አሚን ዶ/ር ፋሲል አስረስ እንዳብራሩት በሀገረ ስብከቱ ስር የሚገኙ ምዕመናን፤ ካህናትና ሊቃውንት በቀጣይ ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀ ጠል ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰው የስርጭት ፍትሀዊነትና ታማኒነት እንዲኖረው የየዞኑ ሀገረ-ስብከት ከአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤቶች ጋር ተደጋግፈው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የአማራ ልማት ማህበር እያደረገ የሚገኘውን አስተዋፅኦ አድንቀው ዳያስፖራው ማህበረሰብ የልማት ማህበሩ አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Gallary


The News