“ሰው ከሚጎድለው ገንዘቡ ቀንሶ የተቸገሩትን ያግዛል፤ ገንዘብ በሁላችን ላይኖር ይችላል፤ ደም ግን በሁላችን አለ…’’ የአልማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

Posted on : May: 16/20
Card image

“ሰው ከሚጎድለው ገንዘቡ ቀንሶ የተቸገሩትን ያግዛል፤ ገንዘብ በሁላችን ላይኖር ይችላል፤ ደም ግን በሁላችን አለ…’’ የአልማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ

“ሰው ከሚጎድለው ገንዘቡ ቀንሶ የተቸገሩትን ያግዛል፤ ገንዘብ በሁላችን ላይኖር ይችላል፤ ደም ግን በሁላችን አለ…’’ የአልማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የዋናው መስሪያ ቤት ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ግንቦት 6/2012 በቢሯቸው ደም ለግሰዋል፡፡ የአልማ ራዕይ በክልሉ የራሱን የልማት ችግሮች በራሱ አቅም የሚፈታ ማኅበረሰብ ተፈጥሮ ማዬት ነው፡፡ የማኅበሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ መዝገበ አንዷለም እንዳሉት ልማት ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ቢሆንም ሕዝብ በቀላሉ አዋጥቶ አካባቢውን ሊያለማ ይችላል፡፡ እናም አልማ ህዝቡን በማስተባበር ረገድ በክልሉ ተምሳሌት ነው፡፡ የማኅበረሰብን ጤና መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡በደም እጦት የሚሰቃዩ እና ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ የብዙዎች ችግር የሆነውን የደም እጥረት ብዙዎች ተሰባስበው በቀላሉ ሊፈቱት እንደሚችሉም አስገንዝበዋል፡፡ “ሰው ከሚጎድለው ገንዘቡ ቀንሶ የተቸገሩትን ያግዛል፤ ገንዘብ በሁላችን ላይኖር ይችላል፤ ደም ግን በሁላችን ስላለ ምንም ሳይጎድልብን በደም እጦት ለተቸገሩ መድረስ የሚሰጠን ውስጣዊ ሀሴት ከፍተኛ ነው” በማለት ደም መለገስ ገንዘብን ወይም ቁስን ከመስጠት በተለዬ ሕይወትን ለማትረፍ የሚበረከት ውድ ስጦታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አልማ በደም ዕጥረት ምክንያት የሚሰቃዩና ሕይወታቸውን የሚያጡ በርካቶች መሆናቸውን በመረዳት በጎ ፈቃደኞች ደም እንዲለግሱ እየቀሰቀሰም ነው፡፡ የአልማ አባላት ልማትና የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ዳይሬክተር ጌቴ ሙላቱ እንዳሉት በርካርታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ደም ለመለገስ ፈቃደኛ ሆነው ኮሮና ወረርሽኝን በመፍራት ላይሰጡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከመፍራት ይልቅ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ በደም እጦት ህይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉትን ማዳን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ማህበሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ደም በበጎ ፈቃደኝነት እንዲለግሱ ቤት ለቤት ተንቀሳቅሰው የሚቀሰቅሱና ግንዛቤ የሚፈጥሩ በጎ ፈቃደኞችን አሰማርቶ ህብረተሰቡ ባለበት አካባቢ ሆኖ እንዴት እና በምን መልኩ ደም መለገስ እንደሚቻል ከደም ባንክ ጋር በመነጋገር ወደስራ ገብቷል፡፡ አልማ የክልሉን የልማት ችግር ለመፍታት እያከናውናቸው ካሉ ዐበይት ተግባራት ባለፈ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር እየሠራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ የደም እጥረት ችግሩን ለመፍታት በዕቅድ እየሠራ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ አልማ በክልሉ 150 ወረዳዎች እና በሁሉም ቀበሌዎች ለበጎ ፈቃደኞች ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ በየቅርንጫፉ ያሉ ሠራተኞቹ ደም እንዲለግሱ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

Gallary


The News