ለአማራ ባህል ማእከል ግንባታ እስካሁን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የአማራ ልማት ማኅበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Posted on : May: 23/21
Card image

ለአማራ ባህል ማእከል ግንባታ እስካሁን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የአማራ ልማት ማኅበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ለአማራ ባህል ማእከል ግንባታ እስካሁን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የአማራ ልማት ማኅበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለዘመናት በሀገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ ድርሻ ያለውን የአማራ ሕዝብ ባህል፣ ቅርስ፣ እሴት እና ትውፊት የሚገልጽ የባህል ማእከል በአዲስ አበባ አልነበረውም፡፡ በአዲስ አበባ የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ሲካሄድ መቆየቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪና የአልማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተባባሪ አቶ ጃጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡ ማእከሉ አብሮነትን እና ኢትዮጵያዊነትን በአዲስ አበባ የምንገነባበት ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር በከተማዋ የሚገኙ የአልማ ከ46 ሺህ በላይ አባላት እና ደጋፊዎቹ በማንነታቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም ከ34 ሚሊየን ብር በላይ አበርክተዋል ብለዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ የሰፊ ባሕል እሴት እና ትውፊት ባለቤት ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር የባህል ማእከል ግንባታው አበርክቶውን እና ልዕልናውን በሚመጥን ደረጃ ይሆናል ተብሏል፡፡ ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

Gallary


The News