“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Posted on : May: 23/21
Card image

“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማእከሉ ግንባታ የሚያርፍበትን ካርታ ለአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል፡፡ “ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች በተለያዩ ስያሜ የተደራጁ የልማት ተቋማት ከሚሞሉት የመሰረተ ልማት ክፍተት በላይ ለአብሮነታችን ዋልታ ናቸው ብለዋል፡፡ "ሽህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሽህ" የሚለው የአልማ መልዕክትም ለአብሮነታችን መቆሙን ያመላክታል ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚሠሩ የልማት ተቋማት ተቀራርበው እንዲሠሩ፣ ሕዝቦቻቸውን እንዲያቀራርቡ እና በጋራ የሀገር ግንባታ ሂደት ጉልበት እንዲሆኑ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ከሚያለያዩን ውስን ጉዳዮች ይልቅ አንድ በሚያደርጉን እልፍ ጉዳዮቻችን ላይ በጋራ እንሠራለን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፡፡ አዲስ አበባንም የኢትዮጵያዊያን የልማት እና የቱሪዝም ማእከል ለማድረግ ይሠራል ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ በዌብሳይት www.amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Gallary


The News