"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Posted on : May: 23/21
Card image

"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ መርኃግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተዋል፡፡ በመርኃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)ን ግብሩ እንደ ስሙ የተጣጣሙለት የልማት ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማልማት ፍቅር፣ ይቅርታ እና መደጋገፍ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለንን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ለማልማት ሕብረት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሁናዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ በርካታ ፈተናዎች ፊት ለፊት የተጋፈጡበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰው የፈተናዎቿ ምንጭ ደግሞ ለመለወጥ፣ ለመልማት እና ለማደግ የምታደርገውን ጥረት ያልፈለጉ ኃይሎች የሚፈጥሩት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ድኃ እናት ጀርባ ሌሎች ተንጠላጥለው የሚያድጉባት ሀገር አይደለችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም" ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ በዌብሳይት www.amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Gallary


The News