የአማራ ልማት ማህበር በክልሉ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የምግብና የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

Posted on : October: 28/20
Card image

የአማራ ልማት ማህበር በክልሉ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የምግብና የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

ልማት ማህበሩ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚሰጠውን 12 ሺ 500 ባለ 50 ሉክ ደብተር፤12 ሺ 500 እስክርፒቶና 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄት በዙኑ ለተቋቋመው የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ ሀይል ዛሬ አስረክቧል፡፡ በብሄረሰብ ዞኑ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ -ሀይል አባልና የምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ መሀመድ ይማም በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት የአንበጣ መንጋው በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው የአማራ ልማት ማህበር ከተጎጅው ህብረተሰባችን ጎን ቆሞ አደጋውን ለመቆቋም የሰጠው ፈጣን ምላሽ ከዞኑ ህዝብ ልብ ዘንድ ከፍተኛ ቦታ አለው ብለዋል፡፡ የአማራ ልማት ማህበር ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ አቶ አበባው ታደሰ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት በበኩላቸው አልማ በዘላቂነት የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ ራዕይ ቀርፆ ከመንቀሳቀስ ባሻገር ለሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሮ አደጋዎች ፈጥኖ ምላሽ የመስጠት አቅሙን ለማጠናከር መላው የክልላችን ህዘዝብ፤ የውጭና የሀገር ውስጥ አጋር ድርጅቶች ፤በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች በገንዘብ፤ቁሳቁስና በዕውቀት ሊደግፉት ይገባል ብለዋል፡፡

Gallary


The News