በአሜሪከ አውሮፓና መከከልኛው ምስራቅ የሚገኙ የአማራ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስተባባሪዎች አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል የማህበራዊ ተቋማት ያደረሰወን ጉዳት መልሶ በማቋቋም ሂደት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ በትጋት እየሰሩ መሆናቸውነ ገለፁ፡፡

Posted on : October: 09/21
Card image

በአሜሪከ አውሮፓና መከከልኛው ምስራቅ የሚገኙ የአማራ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስተባባሪዎች አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል የማህበራዊ ተቋማት ያደረሰወን ጉዳት መልሶ በማቋቋም ሂደት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ በትጋት እየሰሩ መሆናቸውነ ገለፁ፡፡

ዘጠኝ አባላት ያሉትና በአሜሪካ ፤አውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ የማህበሩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስተባባሪዎች ሰሞኑን በአዲስ አበባ የአልማ ጽ/ቤት ስራ ሃላፊዎች ጋር ባካሄዱት የውይይት መድረክ ላይ እንደገለፁት ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መሪ ቃል ቀይሶ መንቀሳቀስ ከጀመረ ወዲህ ዳያስፖራው ማህበረሰብ ራሱን አደራጅቶ ከስትራቴጂክ እቅዱ ጋር በተጣጣመ መልኩ በክልሉ የሚታየውን የትምህር ቤቶች የጥራት ደረጃ ካለበት 16 ፐርሰንት ወደ 50 ፐርሰንት ከፍ ለማድረግ ያከናወናቸውን አስተዋፅዎች በዝርዝር ጠቅሰዋል፡፡ የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በሰ/አሜሪካና በእንግሊዝ ባደረጋቸው የመስክ ጉብኝቶችና ውይይቶች ወቅት ዳያስፖራው በክልሉ የሚታዩ ማህበራዊ ልማት ክፍተቶቸን ለመደገፍ ያሳየውን ፍላጎት ተከትሎ ከማህበሩ የለውጥ ዕቅድ ከጀመረበት ወዲህ በዳያስፖራው ተሳትፎ በደ/ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ በ26 ሚለየን ብር ወጭ የተገነባው የሲራክ ጫኔ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፤ በአትላንታ ጂዮርጂያ አልማ ቅርንጫፍ ማህበር አማካይነት በወልዲያ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኘው የየጁ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የG+2 የ18 ክፍሎች መማሪያ ክፍል ግንባታ የዳያስፖራው ተሳትፎ ማሳያዎች መሆናቸውን የውይይቱ ተሳታፊዎቸ በአስረጅነተ አንስተዋል፡፡ በእንግሊዝ ሀገር የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በሰ/ሸዋ ዞን ፣ በባሶና ወራና ወረዳ፣ በግፍት ቆላ ቀበሌ የሚገኘውን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጥራቱን የማስጠበቅ ስራ መጀመሩን የጠቀሱት የአዲስ አበባ አልማ ፅ/ቤት አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በምስ/ጎጃም ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በአስቴሪዮ ቀበሌ ሊገነባ የታሰበው የአስቴሪዮ የመጀመሪያ ት/ት ቤትን ለማስጀመር በሂደት ላይ መሆኑን ለዳያስፖራ ቡድኑ መረጃ ሰጥተዋል፡፡ ዳያስፖራው አባላት ተደራጅቶ የአማራ ክልል ልማት አጋር ለመሆን ከአማራ ልማት ማህበር ጋር በሚያደርገው የትብብርና ማህበራዊ ልማት ድጋፍ መቀመጫውን አሜሪካን ሀገር ያደረገው ወንፈል ተራድኦ ድርጅት ከቡክ ፎር አፍሪካ ከተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚውሉ 3 ኮንቴይነር የማጣቀሻ መጽሀፍትን ድጋፍ አድርጓል፡፡ በጤናው ዘርፍም ቢሆን በካናዳ ሀገር የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በአቶ ከበደ ኃ/ማርያም አስተባባሪነት ግምቱ ከ7 ሚሊ ብር በላይ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ለኮምቦልቻ ሆስፒታል አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን በአውስትራሊያ የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ለወልዲያ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ አድርገዋል፡፡ የዳያስፖራ አባላቱ አልማ በማህበራዊ ልማት የሚያደርገውን ጥረት ከመደገፍ ጎን ለጎን አሸባሪው የትህነግ ቡድን በክልሉ ነዋሪወች ላይ ያደረሰውን መፈናቀልና ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ በመገንባትና በቁሳቁስ በማሟላት የጀመሩትን ድጋፍ አጠናቅረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት የተፈናቀሉ ወገኖችን በተመለከተ በጃፓን ሀገር የሚገኘው የአዴይ አበባ ኢትዮጵያ ማህበር 5,482 ዶላር እንዲሁም በኳታር የሚገኙ የአልማ አባላት 2,962 ዶላር፣ በጅዳ የሚገኙ የአልማ አባላት አልባሳትን፣ በጣሊያን ሀገር የሚገኙ የአልማ አባላት 1 ኮንቴይነር የህክምና እና የምግብ ቁሳቁሶችን በአልማ በኩል ልከው ለተጠቃሚው ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተመልክቷል፡፡ ሂዩማን የተባለው ግብረ-ሰናይ ድርጅት 3 ኮንቴይነር የህክምና ቁሳቁስ በአማራ ክልል በአሸባሪው ትሀነግ ወራሪ ቡን ለተጎዱ የጤና ተቋማት የሚውል ድጋፍ ወረታ ወደብ ደርሶ በቅርቡ ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ የአዲስ አበባ አልማ ጠቅሷል፡፡ አልማ ዳያስፖራውን የሚያስተባብሩ ቅርንጫፍ ማህበራት በሰ/አሜሪካ (በ7 ግዛቶች)፣ በእንግሊዝ፣ በመካከለኛው ምስራቅ (በኳታር፣ ጅዳ፣ ዱባይ)፣ በጀርመን፣ በጣልያን፣ በጅቡቲ፣ በሱዳን ፣ በካናዳ፣ ከፍቶ ወደ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል፡፡ ዳያስፖራ አባላቱ በቀጣይም ከአማራ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ክለሉን ህዝብ ለመደገፍ ከሚያደርጉት ተሳትፎ ጎን ለጎን ራሳቸውን ጠቅመው ክልላቸውንና አገራቸውን ሊጠቅሙ በሚችሉ ፕሮጀክቶች ለመሳተፍ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ የዳያስፖራ አመራሮች 1) አቶ መንግስቱ ሞት ባይኖር----------- የሰ/አሜሪካ የአልማ ቦርድ ሰብሳቢ 2) አቶ ተሻገር መንገሻ ------------------- የአትላንታ ጂዮርጂያ አልማ ቅ/ማህበር ም/ ሰብሳቢ 3) አቶ ከበደ ኃ/ማርያም ----------------- በካናዳ ባንኮቨር ከተማ የአልማ አስተባባሪ 4) አቶ ላእከ ማለደ ---------------------- የአትላንታ ጂዮርጂያ አልማ ቅ/ኮሚቴ አባል 5) አቶ ዛይድ ይማም ------------------ የአትላንታ ጂዮርጂያ አልማ ቅ/ኮሚቴ አባል 6) አቶ አለባቸው አደመ ---------------- የአትላንታ ጂዮርጂያ አልማ ቅ/ኮሚቴ አባል 7) አቶ ለማ አታክልቴ -------------------- የዲሲና አካባቢው አልማ ቅ/ማህበር ሰብሳቢ 8) አቶ ሀብታሙ አሳዬ ------------------- በኳታር የአልማ ቅ/ማህበር ሰብሳቢ 9) አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ ------------------- በጀርመን የአልማ ቅ/ማህበር ሰብሳቢ ናቸው፡፡ 10) አቶ ሀሚድ አህመድ የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ 11) አቶ ሰለሞን ጉታ የዳያስፖራ የበጎ ፈቃድና አጋር አካላት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት 12) አቶ መንበሩ አውደው የዳያስፖረራ ቡድን መሪ ናቸው፡፡

Gallary


The News