በየደረጃው የሚገኘው የአማራ ልማት ማህበር መዋቅር በሞራልም ሆነ በህግ ከስልጣን ተባሮ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራው ትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀላቸው ወገኖቻችንን በማቋቋምና የትምህርት ተቋማትን ደረጃ በማሻሻል እንሰራለን ሲሉ ገለፁ፡፡

Posted on : October: 11/21
Card image

በየደረጃው የሚገኘው የአማራ ልማት ማህበር መዋቅር በሞራልም ሆነ በህግ ከስልጣን ተባሮ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራው ትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀላቸው ወገኖቻችንን በማቋቋምና የትምህርት ተቋማትን ደረጃ በማሻሻል እንሰራለን ሲሉ ገለፁ፡፡

ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር የሚገኙ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች ማህበሩ በባህር ዳር ከተማ ባዘጋጀው የ2013 ዓ.ም አፈፃፀምና 2014 ዓ.ም ዕቅድ ምክክር መድረክ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት በሁለት አመት የስትራተጅያዊ የለውጥ ዕቅዱ ቁልፍ ችግር ተብለው በተለዩት የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል ላይ ያሳየው ዕምርታ እጅግ ጠቃሚ እንደነበር አውስተው ዘርፉ ለክልላችን ዕድገትና ዘላቂ ልማት ወሳኝ የመሆኑን ያህል የአባላትን ህዝባዊ መሰረት በማስፋትና የማስፈፀም አቅም ውስንነት ታይቷል ብለዋል፡፡ ክፍተቱን በቀጣይ ለማሻሻል ልማት ማህበሩ በ2014 ዓ.ም ያፀቀደውን የዘላቂ ልማትና በአሸባሪው ትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ የማቋቋም ተግባር በሙሉ አቅም መደገፍ የሚያስችል የልማት ሀብት ለማንቀሳቀስ የማህበሩን ህዝባዊ መሰረት የማስፋት ስራ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የጋራ አቋም ወስደዋል፡፡ ሰብዓዊ ሀብታችን ችግር ውስጥ በገባበት ወቅት ማህበሩ ይዞት የቀረበው ዕቅድ በክልሉ ህዝብ ፤መንግስትና ማህበሩ ጠንካራ አመራር ይሳካል ያሉት የመድረኩ መሪ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊና የአማራ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዶ/ር ማተቤ ታፈረ የአልማ መዋቅር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ከማሻሻል ጎን ለጎን በሞራልም ሆነ በህግ ከስልጣን በተወገደው የትህነግ አሸባሪ ቡድን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ህፃናትና እናቶችን መልሶ በማቋቋም ቅድሚያ ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

Gallary


The News