‘አማራ ሆኖ የአማራ ልማት ማህበር አባል ካልሆነ የምን አባል ሊሆን ይችላል’ ? ዶ/ር ማተቤ ታፈረ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድና የክልሉ ት/ቢሮ ሐላፊ

Posted on : October: 12/21
Card image

‘አማራ ሆኖ የአማራ ልማት ማህበር አባል ካልሆነ የምን አባል ሊሆን ይችላል’ ? ዶ/ር ማተቤ ታፈረ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድና የክልሉ ት/ቢሮ ሐላፊ

ዶ/ር ማተቤ ተፈራ የአማራ ልማት ማህበር አባል ያልሆነ አማራ የምን አባል ሊሆን ይችላል ? ሲሉ ያጠየቁት ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር የሚገኙ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች የ2013 ዓ.ም አፈፃፀምና 2014 ዓ.ም ዕቅድን ለማፅደቅ በባህር ዳር ከተማ ባካሄዱበት የምክክር መድረክ ሲያጠቃልሉ ነው፡፡ የማህበሩ ስራ አመራር ቦርድና የትምህርት ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ማተቤ ታፈረ አማራ ልማት ማህበር ከለውጥ ዕቅድ በፊት ባሉት አስር አመታት የተጓዘበትን የልማት ሀብት አሰባሰብ በሁለት የስትራተጅያዊ አመታት ብቻ ማንቀሳቀስ መቻሉ ክልላችን ውስጥ ለዘላቂ ልማትና ሀገራዊ ብልፅግናች መሰረት የሚሆን ያልተጠቀምንበት በርካታ አቅም መኖሩን አመላካች ነው ብለዋል፡፡ ልማት ማህበራችን እያከናወነ የሚገኘውን ዘላቂ ልማት ለሁሉም ባለድርሸ አካላት ማስገንዘብና ልማትን በሚደግፍ መንገድ ማደራጀት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አልማ ተቋማዊ ራዕይና ግብ በሚፈለገው የድጋፍ መጠን መግባባትና መተማመን በመፍጠር በቀጣይ ያለፈውን ጊዜ ሊያካክስ የሚያስችል ህዝባዊ መሰረት የማስፋት፤ የትምህርትና ጤና ፕሮጀክቶችን ማስፈፀም የሚያስችል የልማት ሀብት ማንቀሳቀስ እንዲችል በሙሉ ልብ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ዶ/ር ማተቤ አስገንዝበዋል፡፡ የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሀሪ በበኩላቸው አልማ በክልላችን ከሚገኙ ሲቪክ ተቋማት ትልቁና የህዝብና መንግስት ሙሉ አቅም እያንቀሳቀስ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ፤ለህልውና ዘመቻ አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ እየተጠቀምን በምንገኘው ልክ የተደራጀ ህዝባችንን ለዘላቂ ልማት ግንባታ እንደሚውል ገልፀዋል፡፡

Gallary


The News