የወረዳው አመራር ከመደበኛ ተልዕኮው ጎን ለጎን የአልማን የለውጥ ዕቅድ ግንባር ቀደም መሪ ሆኖ ሊፈፅም እንደሚገባ የቡሬ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ::

Posted on : October: 27/21
Card image

የወረዳው አመራር ከመደበኛ ተልዕኮው ጎን ለጎን የአልማን የለውጥ ዕቅድ ግንባር ቀደም መሪ ሆኖ ሊፈፅም እንደሚገባ የቡሬ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ::

በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አበጀ ሙላት ይህን የገለፁት የወረዳውን የ2013 ዕቅድ አፈፃፀምና በ2014 በጀት አመት ዕቅድ እንዲሁም በአልማ የሚሰሩ ተግባራትን ገምግሞ ባፀደቀበት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው። የአማራ ልማት ማህበር የቡሬ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ትዕዛዙ አማራ ልማት ማህበረ ከምስረታው ጀምሮ ልዩ ለዩ ስትራተጅያዊ ዕቅዶችን በማዘጋጀት መንግስትን፤ ህዝቡንና አጋር ድርጅቶችን አቅም በማስተባበር የትምህርት ፣ ጤና እና በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ያልተቆጠበ ድገፍ በማድረግ ለይ የሚገኝ አገር በቀል የልማት ማህበር ነው። መንግስት ህብረተሰቡና አልማ ተቀናጅተው በ2013 ዓ.ም በዙሪያ ወረዳ ከደረጃ በታች የሆኑ አጠቃላይ ትምህርት ቤቶችን ገፅታ ደረጃ ለማስጠበቅ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያወሱት ሃላፊው ባለፈው በጀት አመት የተከሰቱት የማስፈፀም አቅም ማነስ፤ የማህበሩ ህዝባዊ መሰረት የማስፋትና ቁርጠኝነት ችግሮችምክንያት የተፈለገውን ያህል ርቀት አልተጓዝነም ብለዋል፡፡ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የአልማ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ደረጀ መኮነን በበኩላቸው የአማራ ልማት ማህበር ስትራተጅያዊ የለውጥ ዕቅድ የአጠቃላይ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ወረዳችን በሰለጠነ የሰው ሀብት ልማት እንዲደገፍ ከተፈለገ በ2013 በጀት አመት የተለዩ ችግሮች በ2014 ዓ.ም እንዳይደገሙና የማህበሩን የለውጥ ዕቅድ የተደራጀ የአመራር ስምሪት በመስጠት የወረዳውን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ይጠይቃል ብለዋል። የዙሪያ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበጀ ሙላት ለመድረኩ እንደገለፁት የወረዳው ሁሉም አመራር የልማት ማህበሩን የለውጥ ዕቅድ ከመደበኛ ተልዕኮ ሳይነጥል ከባለድርሻ አካላት ጋር መተማመንና መግባባት መፍጠር ፤ ህዝባዊ መሰረቱን ማስፋትና የልማት ሀብት መጠኑን በመጨመር የወረዳወን ህዝብ ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋለ። የአመራር መድረኩ ለ2014 ዓ.ም በወረዳው አልማ ቅ/ፅ ቤት የቀረበለትን የልማት ሀብት ማስፈፀሚያ በጀት 13 ሚልዮን 412 ሺ 807 ብር ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

Gallary


The News