በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ ለደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጦርነት ተጎጅ ወገኖች 2 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር ወጭ የተደረገበት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

Posted on : February: 25/22
Card image

በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ ለደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጦርነት ተጎጅ ወገኖች 2 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር ወጭ የተደረገበት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በኢትዮጲያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዋሽንግተን፤ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስና የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁ አቡነ አትናቲዎሰ ድጋፉን ለደቡብ ወሎ ና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊዎች ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት በጎ አድራጊ ወገኖቻችን ሀብት አሰባስቦ ከመላክ ባለፈ የጉደቱን መጠን በቦታው ተገኝተው በአይናቸው ማየትና መረዳት የሚችሉ ተወካይ መላካቸው ችግሩን ለመቅረፍና በትብብር ለመስራት ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡ በዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ የሚኖሩ ምዕመናን፤ ካህናትና ሊቃውንት በቀጣይ ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው የጠቀሱት ብፁ አቡነ ማርቆስ የስርጭት ፍትሀዊነትና ታማኒነት እንዲኖረው የየዞኑ ሀገረ-ስብከት ከአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤቶች ጋር ተደጋግፈው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አመራር ሰጥተዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የዕርዳታ ድጋፉን ከተረጅ ወገኖች ድረስ በማጓጓዝና ወጭውን በመሸፈን የአማራ ልማት ማህበር እያደረገ የሚገኘውን አስተዋፅኦ በእርግጥም ህዝባዊ ማህበርነቱን ያስመሰከረ መሆኑን የጠቁሱት ብፁዕነታቸው በውጭ ሀገርም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙ በጎ-አድራጊዎችና የልማት አጋሮች የልማት ማህበሩ አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአማራ ልማት ማህበር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ በበኩላቸው አልማ ሀይማኖት ፤ቋንቋ ፤ ፆታ፤ ዘርና የሀብት ልዩነት በልማት ለመተባበር ያላገዳቸው 4 ሚሊዮን በላይ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች እንዳለው ጠቅሰው ከጠንካራ አጋሮቹ መካከል የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አንደዷ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ልማት ማህበራቸው በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር የዕለት ደራሽ ምግብና ዘላቂ ማህበራዊ ልማትን አቅዶ በማከናወን ላይ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ በቀጣይ እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንና ሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በጦርነት የወደሙ የትምህርትና ጤና ተቋማትን መልሶ የመገንባት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

Gallary


The News