«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም » የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ
«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም » የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ---------------//////------------- በጎንደር ከተማ አስተዳደር በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባው ባለሁለት ወለል ህንጻ ትምህርት ቤት ተመርቋል ፡፡ በምረቃ ፕሮራሙ ላይ የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፈንታ በንግግራቸው አልማ የራሳችንን ችግር በራሳችን አቅም እንፍታ ብሎ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል። ትልቁ ችግራችን ትምህርት ነው በሚል ጽንሰ ሃሳብ ባለፉት ዓመታት ትምህርት ላይ ሥንሠራ ቆይተናል ብለዋል። እንደ ሥራ አሥፈጻሚው ገለጻ ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም ብለዋል። አልማ ቁልፍ መሣሪያ አድርጎ እየሄደ ያለው ትምህርትን ከለወጥን ሁሉን ነገር መለወጥ ይቻላል፣ የሁሉ ነገር መሠረት ትምህርት ነው ብሎ ያምናል ሲሉ ገልጸዋል። ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ነው የተናገሩት። አልማ ማኅበረሰቡ የእኔ ነው የሚለው ተቋም መኾኑንም ገልጸዋል። የተማርንበትን ትምህርት ቤት እናልማ በሚል ብሂል ምሁራን እየገነቡ መኾናቸውን ነው የተናገሩት። ሁሉንም ማቀናጀት ከቻልን የልማት ችግሮቻችንን እንፈታለን ነው ያሉት። ሁሉም የአልማ ደጋፊዎች ቢኾኑ መልሰው የሚጠቀሙት ራሳቸው መኾናቸውን ነው የተናገሩት። ከትምህርት ቤቶች ባሻገር በጎንደር ከተማ የተገነቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን በአንድ ከተማ ውስጥ ኾነው ነገር ግን የተለያዩ ነዋሪዎችን ያገናኙ ናቸው ነው ያሉት። መሪዎች ሕዝብን በልማት ማሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል። ሕዝብ የልማት ተሳታፊ ሲኾን ልማቱን ይመራዋል ነው ያሉት። ሕዝቡም የልማቱ ተሳታፊ እንዲኾን ጥሪ አቅርበዋል።የመረጃ ምንጭ አሚኮ፡፡ አልማ ፡13/03/2017 ዓ.ም ሺ ሆነን እንደ አንድ ፣አንድ ሆነን እንደ ሺ !