የአማራ ልማት ማህበር በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር ደብረማርቆስ ከተማ ለሚገኘው በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 32 ተማሪዎች የስማርት ስልክ እና የገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡ በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካስፈተናቸው እና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 30 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ሳምሰንግ ሞባይልና ከ38ሽህ ብር በላይ የማበረታቻ ሽልማት ሲሰጣቸው በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 2 ተማሪዎች ደግሞ የሳምሰ ሞባይልና ለእያንዳንዳቸው የ40ሽህ ብር በድምሩ ለ32 ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ፣ የትምህርት ቢሮ ሃላፊና የአልማ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ደ/ር ሙሉነሽ ደሴ ተበርክቶላቸዋል ፡፡ የሽልማት ፕሮግራሙን አስመልክቶ ደ/ር ሙሉነሽ ደሴ በመልዕክታቸው በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ለማበረታታት እና ለበለጠውጤት እንዲተጉ አልማ ያደረገው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚገለጽ አይደልም ፡፡አልማ የልማት ሀብት በማሰባሰብ በክልሉ የትምህርቱን ዘርፍ ለማሳደግ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ለተማሪዎችም በአልማ የተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ ለበለጠ ሀላፊነት በመትጋት ቤተሰብ እና ሀገር የጣለችባቸውን ሀላፊነት በሚገባ ለመወጣት ጠንክረው መማር እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል ፡፡ አልማ ፡18/03/2017 ዓ.ም የአልማ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇👇👇 https://t.me/AmharaDevtAssociation https://web.facebook.com/profile.php?id=100067437643052 ሺ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺ!