የአማራ ልማት ማህበር በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለተጎዳባቸው ሶስት ወረዳዎች የአልሚ ምግብና የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

Posted on : October: 23/20
Card image

የአማራ ልማት ማህበር በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለተጎዳባቸው ሶስት ወረዳዎች የአልሚ ምግብና የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

ልማት ማህበሩ በዞኑ ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለተጎዳባቸው ሀብሩ ራያ ቆቦና ጉባላፍቶ ወረዳዎ ነዋሪዎች የሚታደለውን 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄት፤ 10 ሺ 743 ባለ 50 ሉክ ደብተርና 10 ሺ 743 እስክርቢቶ ለዞኑ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ- ሀይል ዛሬ ያስረከበው ወልድያና አካባቢው በሚገኘው የአልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በመገኘት ነው፡፡ የዞኑ የአመንዝኮ ግብረ-ሀይል አባልና የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ይመር በርክክብ ስነስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት በዞኑ የአንበጣ መንጋ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ አደጋውን ለመቀልበስ የክልሉ መንግስትና የዞኑ ማህበረሰብ በርብርብ ላይ በሚገኝበት ወቅት አልማ ያቀረበልን ድጋፍ የማህበሩን ህዝባዊነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የዞኑ ትምህርት ምክትል መምሪያ ሀላፊና የአመንዝኮ ግብረ-ሀይል አባል የሆኑት አቶ ሰጠ ታደሰ በበኩላቸው አማራ ልማት ማህበር የዞኑን ትምህርት ቤቶች ደረጃ ከማሻሻል ጎን ለጎን በእንደዚህ አይነት ድንገተኛ አደጋ ወቅት ድጋፍ ይዞ መቅረቡ ችግሩን ከመቋቋም ባሻገር ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ ዕጥረት ይደርስባቸው የሚችለውን የስነ-ልቦና ጫናን በመቀነስ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡ የአልማ ወልድያና አካባቢው ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን አምባየ በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ልማት ማህበሩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚንቀሳቀስበት የማህበራዊ ልማት ባሻገር በክልሉ ድንገተኛና ወቅታዊ አደጋዎች ላይ እየሰጠ የሚገኘው ምላሽ ከስትራተጅያዊ ዕቅዱ የሚመነጭ ነው ብለዋል፡፡ የዞኑ አልማ ባለፈው በጀት አመትም 1.3 ሚሊዮን ብር በመመደብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ህዝባዊነቱን ያስመሰከረ መሆኑን የገለፁት አቶ ካሳሁን ፤ የልማት ማህበሩ ቦርድና ማናጅመንት የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እንዳይቸገሩና በሰብላቸው ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወረዳ ነዋሪዎች እንዲደርስ የላከው ድጋፍ እጅግ ወቅታዊና አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

Gallary


The News