የመተማ ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ ።

Posted on : December: 16/20
Card image

የመተማ ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ ።

የመተማ ወረዳ የአማራ ልማት ማህበር ከመደበኛ አባላት በተሰበሰበ 1ሚሊዩን 500ሺ ብር በመተማ ወረዳ ዲቪኮ ቀበሌ የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 ብሎክ አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት አዲስ ህንጻ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን የመተማ ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳለው ባዘዘው ገልጸዋል ። ኃላፊው አክለውም የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ የተከፈተ እና በ2012 ዓ.ም እንዲጀምር የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በፈቀደው መሰረት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ አማራ ልማት ማህበር በስታንዳርዱ መሰረት ግንባታውን ገንብቶ ማጠናቀቁን እና ለምረቃ ዝግጁ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ፡፡

Gallary


The News