አማራ ልማት ማህበር አሜሪካን አገር ከሚገኝና ‘’ ምህረት ሜዲካል ሰፕላይ’’ ከሚባል በጎ ፈቃደኛ ድርጅት ያገኘውን ግምቱ 9.3 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገበት የህክምና ቁሳቁስ ለደጋዳሞት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስረከበ፡፡

Posted on : December: 16/20
Card image

አማራ ልማት ማህበር አሜሪካን አገር ከሚገኝና ‘’ ምህረት ሜዲካል ሰፕላይ’’ ከሚባል በጎ ፈቃደኛ ድርጅት ያገኘውን ግምቱ 9.3 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገበት የህክምና ቁሳቁስ ለደጋዳሞት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስረከበ፡፡

በምክትል ርዕሰ- መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ልማት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ ለደጋገዳሞት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ወርቁ ፈንቴ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ጤና ትልቁ የህብረተሰባችን ችግር መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት በዶ/ር ጥላሁን መኮነን ጎሹ የሚመራውና የአካባቢው ተወላጆች ያደረጉት ርበርብ ይህ የህክምና መዳህኒትና ቁሳቁስ ድጋፍ ሊቀርብ ችሏል ብለዋል፡፡ የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አራጋው ታደሰ በበኩላቸው እያንዳንዱ ሰው አካባቢውን ለማልማት እንደዚሁ ቢነሳሳ አቅም ያላቸው ሰዎች ሊያግዙት እንደሚችሉና ችግሩን ለይቶ ለመፍትሄው ከተረባረበ ከድህነት መውጣት እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡ የደጋዳሞት ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ወርቁ ፈንቴ መድሀኒቱንና የህክምና ቁሳቁስን ድጋፍ በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት መድሀኒቱና የህክምና ቁሳቁሱ በወረዳቸው በአንዲት በጎ አድራጊ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ለሚገኘው አረፋ መድሀኒያለም ጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Gallary


The News