ማህበራዊ ተቋማት ላይ የሚያጋጥሙ የተደራሽነት ችግሮችንና የውስጥ ግብዓት እጥረትን ለመቅረፍ ማህበረሰቡ የአልማ አባል በመሆን የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

Posted on : December: 16/20
Card image

ማህበራዊ ተቋማት ላይ የሚያጋጥሙ የተደራሽነት ችግሮችንና የውስጥ ግብዓት እጥረትን ለመቅረፍ ማህበረሰቡ የአልማ አባል በመሆን የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

አማራ ልማት ማህበር/አልማ/ ከተቋቋመ ጀምሮ በክልሉ የተለያዩ ተግባራትን በመስራት ለማህበረሰቡ አለኝታነቱን እያሳየ የሚገኝ ማህበር ነው፡፡አልማ ከሚሰራቸው ተግባራት በዋናነት ትምህርትና ጤና ላይ ትኩረቱን በማድረግ የተሻለ የትምህርት ጥራት እንዶኖርና ማህበረሰቡ በአካባቢው የጤና ተቋማት እንዲኖሩት ትምህርት ቤቶችንና ጤና ተቋማትን በመገንባት ማህበረሰቡ ያዋጠውን ገንዘብ መልሶ ለማህበረሰቡ እያስረከበ አግልግሎት እንደሰጡ እያደረገ ነው፡፡ ይህን በማስመልከትም በደብረ ማርቆስ ከተማ አልማ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችንና ሰርቶ ለማህበረሰቡ ያስረከባቸውን ተቋማት አፈፃፀም በማስመልከት እንዲሁም በ2013 በጀት ዓመት ሊያከናውናቸው ባቀዳቸው ተግባራት ዙሪያ ከአባላቱ ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ አልማ የተቋቋመበት ዋና አላማ ከማህበረሰቡ ገቢ በመሰብሰብ መልሶ ማህበረሰቡ የሚገለገልባቸውን ማህበራዊ ተቋማት በመገንባት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ነው የሚሉት የምስራቅ ጎጃም ዞን አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዘላለም አንዳርጌ ማህበረሰቡ ይህን በመረዳት የአልማ አባል ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ህዝቡ የአልማ አባል እንዲሆን በየቀበሌው በማወያየት የተሰሩ ስራዎችን ማስጎብኘት ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፡፡አልማን መደገፍ የሚፈልጉ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ወገኖች የልማት ጥሪ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡እኛ የአልማ አባላትም አባል ከማፍራት ጀምሮ የሚጠበቅብንን መዋጮ በወቅቱ በመክፈል ለተግባራዊነቱ ሃላፊነታችንን ልነወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብተው መኳንንት በከተማችን የትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎች ደረጃ አለመሻሻል በትምህርት ጥራቱ ላይ ግንባር ቀደም ችግር ነው፤ይህን ችግር ለመፍታት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪዎች የአልማ አባል እንዲሆኑ መስራት ላይ ክፍተቶች አሉ ይህን ለማስተካከልና ማህበረሰቡ የአልማ አባል እንዲሆን ለማድረግ ማህበረሰቡን ማወያየትና የተሰሩ ተግባራትን ማስጎብኘት ላይ ቅድሚያሰጠን እንሰራለን ብለዋል፡፡ አልማ የከተማውንና የገጠሩን ማህበረሰብ በማሳተፍ በርካታ ትምህርት ቤቶችንና ጤና ተቋማትን ገንብቶ ስራ ላይ እንዲውሉ አድርጓል ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የደብረ ማርቆስ ከተማ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገንባት ማስረከብ የቻለ ማህበር ነው ብለዋል፡፡ ከተማችን ደብረ ማርቆስን ብንወስድ እንኳ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ በተመሰረቱ ሰፈሮች አካባቢ ማህበራዊ ተቋማት ላይ ማለትም ትምህርት ቤትና ጤና ተቋማት የተደራሽነት ችግሮች አሉ እነዚህን ለመፍታት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ የአልማ አባል በመሆንንና የሚጠበቅበትን መዋጮ ቢያዋጣ አልማ ተቋማቱን ገንብቶ እንደሚያስረክበን በተግባር እያሳየ የመጣ ማህበር መሆኑን አቶ ይትባረክ ተናግረዋል፡፡ ሲል የዘገበው የደብረ ማርቆስ ከተማ ህዝብና ሚድያ ግንኙነት ቡድን ነው፡፡

Gallary


The News