በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ክፍለ ከተማ አልማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

Posted on : December: 16/20
Card image

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ክፍለ ከተማ አልማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

በአዲስ አበባ የአዲስ ክፍለ ከተማ አልማ አስተባባሪ አቶ ጀማል መሃመድ እንደተናገሩት የክፍለ ከተማውን ነዋሪዎች በማስተባበር ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ፣ የአልባሳትና ሌሎች ቁሳቁሶችን የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ተደርጓል። ከዚህ በፊት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል። በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነግረውናል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ የአዲስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ያደረጉትን ድጋፍ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር ጀምበሩ ደሴ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች የእለት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል። ችግር የደረሰባቸውን ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም ማኅበረሰቡ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። ዘገባው የአብመድ ነው

Gallary


The News