አልማ፣ መንግስትና ህዝቡ ተቀናጅተው እየተገበሩት በሚገኘው የክልሉ አጠቃላይ ት/ቤቶች ደረጃ የማሻሻል ስራ ከፍተኛ አመራሩና ተቋማት በባለቤትነት እየፈፀሙት መሆኑ ተገለፀ ፤የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ የክልሉን ትምህርት ቢሮ፤ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅትና የክልሉን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በአርዓያነት ጠቅሰዋል፡፡

Posted on : December: 29/20
Card image

አልማ፣ መንግስትና ህዝቡ ተቀናጅተው እየተገበሩት በሚገኘው የክልሉ አጠቃላይ ት/ቤቶች ደረጃ የማሻሻል ስራ ከፍተኛ አመራሩና ተቋማት በባለቤትነት እየፈፀሙት መሆኑ ተገለፀ ፤የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ የክልሉን ትምህርት ቢሮ፤ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅትና የክልሉን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በአርዓያነት ጠቅሰዋል፡፡

አማራ ልማት ማህበር ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ! 2012-2014 በሚል መሪ ቃል የክልሉን አጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ደረጃ ከ16 በመቶ ወደ 50 በመቶ ማሻሻል የሚያስችል ስትራተጅያዊ ዕቅድ ይዞ መንቃሳቀሱ ይታወቃል፡፡ ስትራተጅያዊ ዕቅዱ በክልሉ አመራር ግንባር ቀደም መሪነት የሚፈፀምና አልማ ህዝቡና መንግስት በባለቤትናት እንደሚያስፈፅሙት ታሳቢ ተደርጎ የተቀረፀ መሆኑን ያወሱት አቶ መላኩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮችና መላ ሰራተኞች የወር ደመወዛቸውን በአመት የሚከፈል በመስጠት፤ የተቋም ኮርፖሬት አባል በመሆን፤ ዕቅዱን ታችኛው የተቋሙ አደረጃጀት አውርዶ በባለቤትነት በማስፈፀም አርዓያነት ያለው ሚና እየፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ለህብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን ! በሚል መሪ ቃል የሚመራው የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት መሪ ቃሉን በሚመጥን መንገድ የልማት ማህበሩ የፕላትኒየም ኮርፖሬት አባል፤ ሙያዊ አበርክቶ ከማደረጉም ባሻገር ሰራተኞቹን የማህበሩ አባል በማድረግ ፤ ለማህበሩ እንቅስቃሴዎች ሽፋን የዐየር ሰዓት መድቦ በዜና ዜና ሀተታ ማስታወቂያና ዶክመንተሪ ፊልሞችን በማዘጋጀት የክልሉ አጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አቶ መላኩ አብራርተዋል፡፡ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብበር ቢሮ በበኩሉ የማህበራችንን የፋናንስ አሰራር ወረዳ ድረስ በመደገፍና የተቋማት አባልነት እንዲጠናከር አስተዋፅኦው የጎላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ሌሎች የክልሉ አመራሮችና ተቋማትም የክልሉን የትቤቶች ደረጃ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት እራሳቸውንና ሰራተኞቻቸውን የማህበሩ አባል በማድረግ ከፍተኛ አመራሩ በአርዓያነት የወር ደመወዙን በመስጠት የድርሻውን እንዲያበረክት ማህበሩ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Gallary


The News