የአማራ ክልል ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በከፍተኛ ፈተና ላይ ቢሆንም እንደ አማራ ልማት ማህበር ዓይነት ህዝባዊ ማህበር በመደራጀትና በትብብር ችግሮችን መሻገር እንደሚቻል የብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ገለፁ፡፡

Posted on : January: 15/21
Card image

የአማራ ክልል ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በከፍተኛ ፈተና ላይ ቢሆንም እንደ አማራ ልማት ማህበር ዓይነት ህዝባዊ ማህበር በመደራጀትና በትብብር ችግሮችን መሻገር እንደሚቻል የብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ገለፁ፡፡

የአማራ ብዙሀን መገናኛ ሰራተኞች የአማራ ልማት ማህበር የ2012-2014 ስትራተጅያዊ የለውጥ ዕቅድ ምክክር መድረክ ላይ እንደገለፁት ሚዲያው ለአማራ ልማት ማህበር ራዕይ እንዲሳካ የሚጥረው የሚዲያ ሽፋን ብቻ ለመስጠት ሳይሆን የአማራ ክልል ህዝቦች በማህበራዊ ልማት የመለወጥና መሻሻል ፍላጎታቸው በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ካለው ፅኑ ዕምነትና የዓላማ አንድነት ነው ብለዋል፡፡ ምንም እንኳ ያለፉት አመታት በመንግስት መዋቅራዊ የአሰራር ችግር የአማራ ክልሉ ህዝብ የደረሰበት በደልና አሁንም እየተሻገረ የሚገኘው ፈተና ከፍተኛ ቢሆንም ያለፉ ችግሮች ጎትተው እንዳይጥሉን ትምህርት ወስደን ከአማራ ልማት ማህበር ጎን በመቆም ሁለገብና የተደራጀ ትብብር በመፍጠር የክልሉን ህዝብ ዘላቂ ማህበራዊ ልማት ለማፋጠን ልንሰራ ይገባል ብለዋል የሚዲያ ባለሙያዎች ፡፡ የአማራ ክልል ህዘዝብ ከቀረብነውና የዘላቂ ልማት አጀንዳ ከዘረጋንለት እጅግ ቅንና ተባባሪ ነው ያሉት የአማራ ብዙሀን መገናኛ ጋዜጠኞች ህዝባችንን ወደ ኋላ የሚጎትቱንና ከመስመር የሚያስወጡንን ጉዳዮች ትተን ወደ ፌት በሚያስወነጭፈንን አጀንዳ ላይ በማተኮር የክልሉን ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን ብለዋል፡፡

Gallary


The News