አልማ በሰሜን ጎንደር ዞን በህወሓት ወራራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

Posted on : September: 09/21
Card image

አልማ በሰሜን ጎንደር ዞን በህወሓት ወራራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

የአማራ ልማት ማህበር ህውሃት በከፈተው ጦርነት በሰሜን ጎንደር ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሚሆን የፊኖ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል። ማህበሩ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚውል 230 ኩንታል የፊኖ ዱቄት በደባርቅ ከተማ በመገኘት ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል። የአልማ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ÷ማህበሩ ከአሁን ቀደም በክልሉ ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በመተከል፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎች ማድረጉን አስታውሰዋል። አሁንም በሰሜን ጎንደር ዞን በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ዜጎችን ችግር ለመጋራት በማሰብ ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 230 ኩንታል የፊኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገበ አንዱዓለም በበኩላቸው÷ የተቋሙ ስራ ትኩረት የሚያደርገው ትምህርት ላይ ቢሆንም፣ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በዜጎች ላይ የህልውና አደጋ በመፍጠሩ ማህበሩ ትኩረቱን በወቅታዊ ድጋፍ ላይ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡ ማህበሩ በቀጣይ ለተፈናቃዮች የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ም አስታውቋል:: ዘገባው የኤፍ ቢ ሲ ነው::

Gallary


The News