‘’አልማን የኢትዮጲያ ዩ ኤስ ኤይድ ማድረግ አንዱ የከፍታ መንገዳችን ነው’’ ! (የአልማ -ዩ.ኤስ ኤይድ ፈፃሚዎች)

Posted on : September: 15/21
Card image

‘’አልማን የኢትዮጲያ ዩ ኤስ ኤይድ ማድረግ አንዱ የከፍታ መንገዳችን ነው’’ ! (የአልማ -ዩ.ኤስ ኤይድ ፈፃሚዎች)

አማራ ልማት ማህበር-ዩ ኤስ ኤድ አፈፃፀም የኤች አይቪ ኤድስ ችግሮችን በመፍታትና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተሻለ ክልል መፍጠር እንደሚቻል ያሳየ ነው ሲሉ የፕሮጀክቱ ቁልፍ የባለድርሻ አካላት ገለፁ፡፡ አልማ -ዩኤስ ኤድ ፕሮጀክት የአንድ አመት ጉዞ አፈፃፀም ላይ ለመምከር በዳንግላ ከተማ በጠራው መድረክ የተሳተፉ የክልሉ የጤና፤የኢኮኖሚ ትብብር፤የፕሮጀክቱ ፈፃሚ ባለድርሻ አካላት እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ቆይታው በክልሉ 33 ወረዳዎችና ሁሉም ዞኖች የኤች አይቪ/ኤድስ መከላከል፤እንክብካቤና ህክምና ስራ ላይ የሴክተሩን ክፍተት በመሙላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡ በጤና ቢሮ የኤች አይቪ አይድስ ምርመራ ቡድን አስተባባሪ አቶ ሰዒድ ፈንቴ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ከ9-14 አመት ዕድሜ በሚገኙ ወላጅ አልባ ህፃናት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ ዘላቂ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ በበርካታ ችግር ውስጥ ሆኖ የተፈፀመ ቢሆንም አጠቃላይ ውጤቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ፤ የዩ ኤስ ኤይድ ችፍ ኦፍ ፓርቲ ዶ/ር ካሳ ጥሩነህ ቀጣዩን ጊዜ የተቀናጀ ስራ ለውጤታማ ዕቅድ አፈፃፀምና ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ አልማ የኢትዮጲያ ዩ ኤስ ኤይድ ማድረግ አንዱ የከፍታ መንገዳችን ነው! ያሉት የፕሮጀክቱ ሁነኛ ፈፃሚዎች ወይም የባለድርሻ አካላት(LIP) አልማ ፕሮጀክቱን ተቀብሎ በመምራት በኩል እያሳየ የሚገኘው እርምጃ ለአገር ውስጥ ፈፃሚዎች (lips) ለቀጣይ አፈፃፀሞቻቸው ማሻሻልና በቅንጅት በመስራት የተሻለ ክልል መፍጠር እንችላለን ብለዋል፡፡

Gallary


The News