አደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበር 340 በአሸባሪው ትህነግ ተፈናቀለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ እናቶችና ህፃናት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡

Posted on : September: 25/21
Card image

አደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበር 340 በአሸባሪው ትህነግ ተፈናቀለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ እናቶችና ህፃናት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡

ጃፓን ሀገር የሚገኘው አደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበር ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ያሰባሰበውን 608 ሺ የጀፓን የን ወይም 249 ሺ 355 የኢትዮጲያ ብር የሚገመት በአሸባሪው ትህነግ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኞች የሚውል ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ድጋፉ ከሰሜን ወሎ ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ጦሳ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተጠልለው ለሚገኙ በቁጥር 450 እማዎራዎችና ህፃናት እንዲሰጥ ለጋሾች በጠየቁት መሰረት 850 ሊትር ዘይት እና 42.5 ኩንታል ሩዝ ግዥ ተፈፅሞ በአማራ ልማት ማህበር በኩል በእለቱ ርክክብ ተደርጎ ለተፈናቀሉ ዜጎች ተሰራጭቷል፡፡ ድጋፉ የድረሳቸው አስተያየት ሰጭዎች እንደገለፁት አማራ ልማት ማህበር ጃፓን ሀገር የሚገኘውን አደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበርን በማስተባበር ያደረገው ድጋፍ እጅግ ጠቃሚና በክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ነው ብለዋል፡፡ በአማራ ልማት ማህበር ደሴ አካባቢ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ርክክብ ያደረጉት ማህበር የአማራ ክልል ተወላጆችና ኢትዮጲያዊ ዳያስፖራ በትህነግ አሸባሪው ቡድን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ደሴ ለሚገኙ ወገኖች የእለት ደራሽ ምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረሱ፡፡ በአማራ ልማት ማህበር የፋይናንስና ሎጅስቲክስ ዳይሬክተር አቶ ሰጠዋል ደሳለኝ ድጋፉን ሲያስረክቡ እንደገለፁት ፤ ጃፓን የሚኖሩ የአደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበር አባላትና ደጋፊዎች አገራችን በተለይም አማራ ክልል ነዋሪዎች አሸባሪው ሀይል የፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ለሰጡት ፈጣን ምላሽ በተጠቃሚው ህዝብ ስም አመስግነው ሌሎች ወገኖቻችንም ዓራያነቱን ተከትለው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ አልማ ባለፈው አንድ ወር ብቻ በአሸባሪው ትህነግ ሀይል ተፈናቅለው ደቡብ ወሎ ፤ደቡብ ጎንደርና ሰሜን ጎንደር ሊሚገኙ ወገኖች ማቋቋሚያ በ3.7 ሚሊዮን ብር ወጭ 827.5 ኩንታል ፊኖ ዱቄት ማከፋፈሉን አቶ ሰቷል አውስተዋል፡

Gallary


The News