የአማራ ልማት ማህበርን ርዕይ በዘላቂነት እንደሚደግፉ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍል ወደ ትውልድ ሀገራቸው የመጡ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊን ገለፁ፡፡

Posted on : January: 24/22
Card image

የአማራ ልማት ማህበርን ርዕይ በዘላቂነት እንደሚደግፉ ከልዩ ልዩ የዓለም ክፍል ወደ ትውልድ ሀገራቸው የመጡ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊን ገለፁ፡፡

አማራ ልማት ማህበር ከዳያስፖራ ማህበረስብ ጋር ለመምክር በጎንደር ከተማ ሀይሌ ሪዞርት ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተገኙ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን እንደገለፁት በዲፕሎማሲ፤ በኢንቨስትመንትና የአገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም ማጎልበት፤ ሀገራቸውን ከመደገፍ ባሻገር ‘’ ማህበራዊ ችግሩን በውስጥ አቅም መፍታት የሚችል የአማራ ክልል ህዝብ ተፈጥሮ ማየት!’’ በሚል ራዕይ የሚመራውን አልማ ዘላቂ አባል በመሆን በቁሳቁስ ፤ገንዘብና ዕውቀት የሚደግፉ መሆኑን ማህበሩ ባዘጋጀው የቃል-ኪዳን መመዝገቢያ ቅፅ ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል፡፡ የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ከተለያዩ የአለማችን ክፍል ተጉዘው ወደ ሀገር ቤት ከገቡ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊን መካከል 600 ያህሉ በማህበሩ አድራሻ መመዝገቢያ ቅፅ ሙሉ መረጃቸውን ያሰፈሩ ሲሆን ቁጥራቸው ከአንድ መቶ ሀምሳ የሚልቁት ደግሞ በዘላቂ አባልነት በመመዝገብ የገንዘብ ቁሳቁስና በቴክኒዮሎጅ ሽግግር የልማት ማህበሩን ርዕይ ለመደገፍ የቃል ኪዳን ፊርማቸውን አስቀምጠዋል፡፡ የምክክር መድረኩን የመሩት የአልማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ መላኩ ፈንታ አገሪቱ በለውጥ ምዕራፍ ከጀመረች ወዲህ ዳያስፖራው ማህበረስብ በልማት ማህበሩ ዘላቂ ልማት ላይ እያበረከተ የሚገኘውን አስተዋፅኦ አድንቀው የክልሉ ህዝብ በሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች በተፈተነበት ወቅት ቀድሞ በመድረስ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡ ‘’ሀገሬ ስትጠራኝ አልቀርም!’’ ብላችሁ የግል ጉዳያችሁን ወደ ጎን ትታችሁ ወራሪ ሀይል በወገናችሁ ላይ ያደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ቦታው ድረስ በመጓዝ በአይናችሁ አይታችኋል ያሉት ክቡር አቶ መላኩ፤ ወገናችሁን መልሶ በማቋቋም ሂደት ከመንግስትና አልማ ጋር በመቀናጀት ለመስራት ለሰጣችሁት ይሁንታ በልማት ፣ማህበሩ ተጠቃሚ ህዝብ ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Gallary


The News