የመጭው ትውልድ ከተማ ! ከአማራ ልማት ማህበር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን

Posted on : January: 11/23
Card image

የመጭው ትውልድ ከተማ ! ከአማራ ልማት ማህበር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን

በአገራችን የከተሞች ዕድገት ታሪክ እጅግ ፈጣን ከሚባሉት ተርታ በግንባር ቀደም ትጠቀሳለች፡፡ ስለ አመሰራርቷ በርካታ መላምቶች የተሰነዘሩ ቢሆንም ከጎጆ ቤት ወደ ትንንሽ መንደሮች ፤ ከትናንሽ መንደሮች ወደ ከተማነት ማዕረግ እያደገች ስለመምጣቷ የGPS (Global Positioning System/ መረጃ ይጠቁማል፡፡ በ1930 ዎቹ ጀምሮ በከተማ አስተዳደር እንድትመራ ከጎጃም ከተሞች አንዷ ሆና ተመዝግባለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት የአማራ ብሄራዊ ክልል ርዕሰ -መዲና ነች፡፡ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ይኖርባታል፡፡ የመንገዶቿ ስፋትና ልስላሴ በመንገዶቿ ግራና ቀኝ የተተከሉት ዘንባባዎቿ ቦታ አያያዝና ውበት የነዋሪዎችን ብቻ ሳይሆን የእንግዳ ደራሽን ቀልብ ይማርካሉ፡፡ ስለ ባህርዳር ከተማ የተፈጥሮ ውበት ለመግለፅ አንዳንዶቹ ቃላት ያጥረናል ሲሉ፤ አይ ባለቅኔ መሆን ይጠይቃል ! የሚል አስተያየት የሚሰጡ ብዙ ናቸው፡፡ በዕርግጥም ፡ እንደ ስጋጃ በከተማዋ ሰሜናዊ አቅጣጫ የተንጣለለው በአፍሪካ ትልቁ የጣና ሀይቅ፤ እንደ መቀነት ወገቧን ሸብ አድርጎት ረጅም ጉዞን የሚቀጥልው ትልቁ አባይ ወንዝ ለከተማዋ ውበት ለዕድገቷ ግርማ ሞገስ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት በኮተቤ ዩኒቨርስቲ ለረጅም ጊዜ በስነ-ፁሁፍ መምህርነት ያገለገሉት ፕሮፌሰር ደርበው አዱኛ ባህርዳርን ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ ስለባህርዳር፤ የምትሄዱ ሰዎች የምትሻገሩ፤ ውብ እሷ ብቻ ነች ብላችሁ ንገሩ፡፡ ሲሉ በጉዞ ማስታወሻቸው ማስፈራቸው የባህርዳር ውበት ምንያህል እንደመሰጣቸው ያሳያል፡፡ በ1990 ዎቹ አመታት በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ሁለተኛ ከተማ በሆነችው ማራካሸ ከተማ ዩኒስኮ ባዘጋጀው ‘’ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው የተመቹ ለመሆን በሚያደርጉት ጥረት ውድድር’’ ከአህጉሪቱን ከተሞች ብልጫ አግኝታ የወቅቱ ከንቲባ ዋንጫ ተቀብሎ መመለሱ ይታሳል፡፡ ባህርዳር ከተማችን፡፡ ሙዚቃ የዘንባባ ማር ነሽ ንቦች የቀሰሙሽ በጥላሁን ገሰሰ ባህርዳር የተፈጥሮ ውበቷ የፈጠረላት ምቹ ሁኔታ ከከተማዋ የዕድገት ፕላን ጋር ተሳስሮ የምታጓጓ ትሁን እንጅ ማህበራዊ ተቋማቶች መካከል የአጠቃላይ ት/ቤቶች የደረጃ ጥራት ግን እጅግ አሳሳቢና ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ችግር ሆኖ ይስተዋላል፡፡ በባህርዳር ከነዚህም ማህበራዊ ልማት ችግሮች መካከል አንዱ የትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ዝቅተኛ ደረጃ ነው፡፡ በባህርዳር ከተማ ባለቤትነታቸው በህዝብ ፣ በግል ባለሀብትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚተዳደሩ 160 የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ፡፡ በነዚህ ት/ ቤቶች ውስጥ 110 ሺ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ፡፡ ት/ቤቶቹ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የመማር ማስተማር ሂደት የሚከናወንባቸው ናቸው፡፡ የትምህርት ቋማቱ ውስጣዊና ውጫዊ ገፅታ በግንባታ ፣ግብዓትና ሂደት ረገድ የፌደራል ትምህርት ሚኒስትርም ሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያስቀመጠውን ደረጃ ያሟሉ አለመሆናቸውን ማሳየትና የመፍትሄ አቅጣጫ መጠቆም የዚህ ዝግጅት ዋና አላማ ነው፡፡ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ 160 ትምህርት ቤቶች መካከል የሚጠበቅባቸውን ደረጃ ያሟሉ 11 በመቶ ብቻ ናቸው እንደ ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀይለማሪያም ፡፡ ቀሪዎቹ 89 በመቶ በግንባታ ፣ ግባዐትና ሂደት ከደረጃ በታች ናቸው፡፡ የነገ አገር ተረካቢ ህፃናት በአካልም ሆነ በአዕምሮ የሚገነቡበትና የትውልድ ሽግግር የሚያደርግባቸው ትምህርትቤቶቻችን የሚገኙበት ደረጃ ታዳጊዋን ከተማና ነዋሪዎቿን የማይመጥኑ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪና አሸማቃቂ መሆናቸውን የትምህርት ባለሙያዎች ፣ የትምህርት አመራሮች፣ ወላጆች፣ተማሪዎችና ነዋሪው ህበረተሰብ በቁጭት ይናገራሉ፡፡ የነገ አገር ተረካቢ ህፃናት በታዳጊዋ ባህርዳር ከተማ ዕውቀት የሚቀሰምባቸውና የትውልድ ርክክብ የሚደረግባቸው የትምህርት ተቋማት ደረጃቸውን አልጠበቁም ስንል የት/ቤቶች ግንባ ፤ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ገፅታ ለህፃናት ሳቢና ማራኪ አለመሆንን ፣ አጥር አልባ ሆኖ ይስተዋላል፡፡ አንዳንድ ት/ቤቶች መቀመጫ ወንበርና ጠረጴዛ የሌላቸው፣ ተማሪዎች አግዳሚ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ለመማር የሚገደዱባቸው ናቸው፡፡ በባህርዳር ሙቀት ጣራውና ግድግዳው ቆርቆሮ በቆርቆሮ በሆነ ቤት የመማር ማስተማር ሂደቱን ማከናወን እጅግ አሰልች ነገር ግን የባህርዳር ከተማ ት/ቤቶች አስከፊ ገፅታ ነው፡፡ ተማሪዎች በዕረፍት ሰዓት ለመፀዳዳዳት የሚቸገሩበት፣ አንዳንዶቹ ጭራሽም መፀዳጃ ቤት የሌላቸው ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ት/ቤቶች የተማሪና ከፍል ፤ የተማሪና ወንበር፣ የተማሪና መፃህፍት ጥምርታ የሚባል የትምህርት ቢሮ ስታንዳርድ ማሰብ የማይታሰብበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ምን አይነት የመፍትሄ አቅጣጫ መከተል ያስፈልጋል ? ለሚለው ጥያቄ ባለሀብቶች፣ የከተማዋ አመራሮቻና ወላጆች፣ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የታዳጊዋ ከተማ ትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ዝቅተኛ ደረጃ ከሚያሳስባቸው የአስተዳደር ዕርከኖች አንዱ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት ነው፡፡ ከንቲባ ፅ/ቤቱ የወደፊቱን ትውልድ ከተማ ርዕይ ለማሳካት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የትምህርት ስራን ለህዝብ ፤ለግል ባለሀብቱና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አሻራቸውን እንዲያሳልፉ መደገፍ ማበረታታትና ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት የከተማ አስተዳድሩ ተቀደሚ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ናቸው ፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ከአማራ ልማት ማህበር፣ ከህብረተሰቡ ፣መንግስት፣ ከግል ባለሀብቶችና ሌሎች አጋር አካላት የትምህርትን ተደራሽነት ከማስፋት ጎን ለጎን ጥራቱን ለማስጠበቅ ገብተው እንዲሰሩና ችግሩን በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ በዘላቂነት ለመፍታት መዘጋጀቱን ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገልፀዋል፡፡ አማራ ልማት ማህበር የክልሉን ህዝብ ፤ መንግስትና ሌሎች የልማት ሀይሎች በማንቀሳቀስ ማህበራዊ ችግሮችን በውስጥ አቅም የመፍታት ርዕይ ተልሞ ይንቀሳቀሳል፡፡ የት/ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ አላማ ስኬትም ህብረተሰብን በችግሮች ዙሪያ ያወያያል ፡፡ ችግሮችን ቅደም ተከተል ይሰጣል፡፡ በተለያየ ዘዴ የልማት ሀብት ያሰባስባል፡፡ ፕሮጀክቶችን ይተገብራል፡፡ የማህሩ አባላት ቁጥር ማነስና የልማት ሀብት ዕጥረት እንጅ በዚህችው ታዳጊ ከተማም አማራ ልማት ማህበር የልማት መነሻ ያህል መስከረም አስራ ስድት፣ በፋሲሎና በፈለገ አባይ ሞዴል ት/ቤቶችን ገንብቶ አሳይቷል፡፡ የአማራ ክልልን ማህበራዊ ችግሮች በውስጥ አቅም እንፍታ በሚል ርዕይ የሚንቀሳቀሰው አማራ ልማት ማህበር የባህርዳን የትምህርት ቤቶች የደረጃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በሚያከናውነው የልማት ሀብት ማሰባሰቢያና የአባል ማፍራት ስራ መላው የባህርዳር ነዋሪዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ አጋሮቹና ወዳጆች ከልማት ማህበራችሁ ጎን ትቆሙ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ Copy Right@

Gallary


The News