The News

የአማራ ልማት ማህበር በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡

Posted on : November: 27/2024

የአማራ ልማት ማህበር ደብረማርቆስ ከተማ ለሚገኘው በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 32 ተማሪዎች የስማርት ስልክ እና የገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡ በክቡር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካስፈተናቸው እና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 30 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ሳምሰንግ ሞባይልና ከ38ሽህ ብር በላይ የማበረታቻ ሽልማት ሲሰጣቸው በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 2 ተማሪዎች ደግሞ የሳምሰ ሞባይልና ለእያንዳንዳቸው የ40ሽህ ብር በድምሩ ለ32 ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ፣ የትምህርት ቢሮ ሃላፊና የአልማ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ደ/ር ሙሉነሽ ደሴ ተበርክ...

Read More

«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም » የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህር ዋና ስራ አስፈጻሚ

Posted on : November: 22/2024

«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም » የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህር ዋና ስራ አስፈጻሚ ---------------//////------------- በጎንደር ከተማ አስተዳደር በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባው ባለሁለት ወለል ህንጻ ትምህርት ቤት ተመርቋል ፡፡ በምረቃ ፕሮራሙ ላይ የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፈንታ በንግግራቸው አልማ የራሳችንን ችግር በራሳችን አቅም እንፍታ ብሎ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል። ትልቁ ችግራችን ትምህርት ነው በሚል ጽንሰ ሃሳብ ባለፉት ዓመታት ትምህርት ላይ ሥንሠራ ቆይተናል ብለዋል። እንደ ሥራ አሥፈጻሚው ገለጻ ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየ...

Read More

«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም » የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ

Posted on : November: 22/2024

«ያልተማረ ትውልድ ሀገር አይለውጥም፤ ያልተማረ ማኅበረሰብ ስለ ልማት መወያየት አይችልም፤ የልማት አጀንዳም አይኖረውም » የተከበሩ አቶ መላኩ ፈንታ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ---------------//////------------- በጎንደር ከተማ አስተዳደር በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባው ባለሁለት ወለል ህንጻ ትምህርት ቤት ተመርቋል ፡፡ በምረቃ ፕሮራሙ ላይ የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፈንታ በንግግራቸው አልማ የራሳችንን ችግር በራሳችን አቅም እንፍታ ብሎ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል። ትልቁ ችግራችን ትምህርት ነው በሚል ጽንሰ ሃሳብ ባለፉት ዓመታት ትምህርት...

Read More

‹‹ በደብተርና እስክርቢቶ ችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ ሊሆን አይገባም፡፡ ›› ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

Posted on : September: 30/2024

‹‹ በደብተርና እስክርቢቶ ችግር ምክንያት አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ ሊሆን አይገባም፡፡ ›› ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) -----------///////----------- የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚገመቱ 100 ሽህ የተማሪ ደብተሮችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ያስረከቡት የአባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ መላሽ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ለሚገኙ በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ለሚኖሩ ተማሪዎች 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት 100 ሽህ ደብተር ለክልሉ ትምህርት ቢሮ አስረክበናል ብለዋል፡፡ ፋብሪካው የተቋቋመበት አንዱ አላማ የትምህርት ስርዓቱን ለመደገፍና ለማገዝ ነው ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ፤ እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ለመሆን ከክልሉና ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ተማሪዎችን ለመደገፍ...

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

Posted on : September: 18/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ። -----------//////-------------- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአልማ ጋር በመተባበር ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው አልባሳትን በጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ። የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ምክትል ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መዝገቡ አንዱዓለም እንዳሉት አልማ ከሚያከናውነው የልማት ሥራዎች ባለፈ በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማሠባሠብ እያደረሰ ይገኛል። አሁንም...

Read More