The News

የአማራ ልማት ማህበር በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ግንባር አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የዕለት ደራሽ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ፡፡

Posted on : August: 31/2021

የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አረጋው ታደሰ እንዳሉት አልማ ህዝቡን ተሳቢ አድጎ የሚሰራ የልማት ተቋም በመሆኑ በአሸባሪው ትህነግ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ለዕለት ምግብ የሚውል 220 ኩንታል ፊኖ ዱቄት በጥቃቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል ፡፡ የደረሰው ጉዳትም ከፍተኛ በመሆኑ አልማ በቀጣይ መንግሰታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶችንና ግለሰቦችን በማስተባባር ለሌሎች አካባቢዎችም ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡አልማ የክልሉ በጎ ፈቃደኞች የልማት ማህበር እንደመሆኑ መጠን በቋሚነት ከሚያደረገው ዘላቂ የማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን ሰው ሰራሽም ይሁን የተፈጥሮ አደጋ በአጋጠመ ወቅት ፈጥኖ ደራሻ መሆኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት አሳይቷል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በአለማቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ...

Read More

"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Posted on : May: 23/2021

"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ መርኃግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተዋል፡፡ በመርኃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)ን ግብሩ እንደ ስሙ የተጣጣሙለት የልማት ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማልማት ፍቅር፣ ይቅርታ እና መደጋገፍ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለንን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ለማልማት ሕብረት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሁናዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ በርካታ ፈተናዎች ፊት ለፊት የተጋፈጡበት ወቅት መሆኑን ጠ...

Read More

“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Posted on : May: 23/2021

“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማእከሉ ግንባታ የሚያርፍበትን ካርታ ለአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል፡፡ “ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች በተለያዩ ስያሜ የተደራጁ የልማት ተቋማት ከሚሞሉት የመሰረተ ልማት ክፍተት በላይ ለአብሮነታችን ዋልታ ናቸው ብለዋል፡፡ "ሽህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሽህ" የሚለው የአልማ መልዕክትም ለአብሮነታችን መቆሙን ያመላክታል ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚ...

Read More

የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ እውን እንዲሆን ኹሉም ድጋፍ እንዲያደርግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀረቡ፡፡

Posted on : May: 23/2021

የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ እውን እንዲሆን ኹሉም ድጋፍ እንዲያደርግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀረቡ፡፡ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአንድነት ፓርክ የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ ሕዝብ ባለፉት ዓመታት እንደሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ጭቆና ሲደርስበት እንደነበር አንስተዋል፡፡ ከድህነቱ በላይ በተነዛበት የሐሰት ትርክት የአማራ ሕዝብ በማንነቱ ምክንያት በየትኛውም ቦታ ተረጋቶ እንዳይኖር ሲደረግ እንደነበረ እና አሁንም ለችግር እየተዳረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የአማራን ሕዝብ ነጥሎ የማስመታት አጀንዳ እንዲዘጋ እና የአጀንዳው ቀጥተኛ ፈጻሚ የሆነውን ኃይል በማስወገድ ሀገራዊ ለውጡ እንዲሳካ የአማራ ሕዝብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከ...

Read More

የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ፕሮጀክት የአማራ ሕዝብ ባሕሉን፣ ወጉን፣ ጀግንነቱን፣ ሃይማኖቱን፣ ቅርሱን እና ሀገር ሠሪነቱን በቋሚነት የሚዘክርበት ነው" የአልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ

Posted on : May: 23/2021

"የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ፕሮጀክት የአማራ ሕዝብ ባሕሉን፣ ወጉን፣ ጀግንነቱን፣ ሃይማኖቱን፣ ቅርሱን እና ሀገር ሠሪነቱን በቋሚነት የሚዘክርበት ነው" የአልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአልማ አባላትና ደጋፊዎች ለማእከሉ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በ1984 ዓ.ም ተመስርቶ በክልሉ ማኅበራዊ ልማትን በመደገፍ የራስን ችግር በራስ የመፍታት አስተሳሰብ አንግቦ እየሠራ የሚገኝ የልማት ማኅበር ነው፡፡ በ2017 ዓ.ም በከፍተኛ ልማታዊ አንድነት የራስን የመልማት ችግሮች በራስ አቅም የሚፈታ ማኅበረሰብ መፍጠር የማኅበሩ ራዕይ ነው፡፡ ማኅበሩ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በአሶሳ የአባላት አደረጃጀት ዘርግቷል፡፡ በውጪ ሀገ...

Read More