The News

"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Posted on : May: 23/2021

"ችግሮች ቢበዙ እና ፈተና ቢበረታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብሩን እና ነፃነቱን ጠብቆ ከመልማት የሚያግደው አይኖርም"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ መርኃግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተዋል፡፡ በመርኃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ)ን ግብሩ እንደ ስሙ የተጣጣሙለት የልማት ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያን ለማልማት ፍቅር፣ ይቅርታ እና መደጋገፍ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለንን ሀብት በአግባቡ ተጠቅመን ለማልማት ሕብረት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሁናዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ በርካታ ፈተናዎች ፊት ለፊት የተጋፈጡበት ወቅት መሆኑን ጠ...

Read More

“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Posted on : May: 23/2021

“ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገነባው የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማእከሉ ግንባታ የሚያርፍበትን ካርታ ለአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል፡፡ “ልማት ድንበር የለውም፤ ልማት የኹላችንም አንድነት እና መደጋገፍ ይጠይቃል” ያሉት ምክትል ከንቲባ አዳነች በተለያዩ ስያሜ የተደራጁ የልማት ተቋማት ከሚሞሉት የመሰረተ ልማት ክፍተት በላይ ለአብሮነታችን ዋልታ ናቸው ብለዋል፡፡ "ሽህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሽህ" የሚለው የአልማ መልዕክትም ለአብሮነታችን መቆሙን ያመላክታል ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚ...

Read More

የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ እውን እንዲሆን ኹሉም ድጋፍ እንዲያደርግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀረቡ፡፡

Posted on : May: 23/2021

የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ እውን እንዲሆን ኹሉም ድጋፍ እንዲያደርግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ጥሪ አቀረቡ፡፡ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአንድነት ፓርክ የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ ሕዝብ ባለፉት ዓመታት እንደሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ጭቆና ሲደርስበት እንደነበር አንስተዋል፡፡ ከድህነቱ በላይ በተነዛበት የሐሰት ትርክት የአማራ ሕዝብ በማንነቱ ምክንያት በየትኛውም ቦታ ተረጋቶ እንዳይኖር ሲደረግ እንደነበረ እና አሁንም ለችግር እየተዳረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የአማራን ሕዝብ ነጥሎ የማስመታት አጀንዳ እንዲዘጋ እና የአጀንዳው ቀጥተኛ ፈጻሚ የሆነውን ኃይል በማስወገድ ሀገራዊ ለውጡ እንዲሳካ የአማራ ሕዝብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከ...

Read More

የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ፕሮጀክት የአማራ ሕዝብ ባሕሉን፣ ወጉን፣ ጀግንነቱን፣ ሃይማኖቱን፣ ቅርሱን እና ሀገር ሠሪነቱን በቋሚነት የሚዘክርበት ነው" የአልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ

Posted on : May: 23/2021

"የአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ ፕሮጀክት የአማራ ሕዝብ ባሕሉን፣ ወጉን፣ ጀግንነቱን፣ ሃይማኖቱን፣ ቅርሱን እና ሀገር ሠሪነቱን በቋሚነት የሚዘክርበት ነው" የአልማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአልማ አባላትና ደጋፊዎች ለማእከሉ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በ1984 ዓ.ም ተመስርቶ በክልሉ ማኅበራዊ ልማትን በመደገፍ የራስን ችግር በራስ የመፍታት አስተሳሰብ አንግቦ እየሠራ የሚገኝ የልማት ማኅበር ነው፡፡ በ2017 ዓ.ም በከፍተኛ ልማታዊ አንድነት የራስን የመልማት ችግሮች በራስ አቅም የሚፈታ ማኅበረሰብ መፍጠር የማኅበሩ ራዕይ ነው፡፡ ማኅበሩ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በአሶሳ የአባላት አደረጃጀት ዘርግቷል፡፡ በውጪ ሀገ...

Read More

ለአማራ ባህል ማእከል ግንባታ እስካሁን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የአማራ ልማት ማኅበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Posted on : May: 23/2021

ለአማራ ባህል ማእከል ግንባታ እስካሁን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የአማራ ልማት ማኅበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለዘመናት በሀገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ ድርሻ ያለውን የአማራ ሕዝብ ባህል፣ ቅርስ፣ እሴት እና ትውፊት የሚገልጽ የባህል ማእከል በአዲስ አበባ አልነበረውም፡፡ በአዲስ አበባ የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ሲካሄድ መቆየቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪና የአልማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተባባሪ አቶ ጃጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡ ማእከሉ አብሮነትን እና ኢትዮጵያዊነትን በአዲስ አበባ የምንገነባበት ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር በከተማዋ የሚገኙ የአልማ ከ46 ሺህ በላይ አባላት እና ደጋፊዎቹ በማንነታቸው...

Read More