የአልማ ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ አበባው ታደሰ እንደገለፁት 308 ሺ ብር ወጭ የተደረገበትንና መስከረም 12/2014 ዓ.ም የአንድ ሴሚሰተር ደብተርና እስክርፒቶ የተደገፉት አንድ ሺ አንድ መቶ ሶስት ህፃናት ተማሪዎችም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን ፕሮጀክቱ አረጋግጧል ብለዋል፡፡ የድጋፉ ተጠቃሚዎች በደሴ፤ ቃሉ፤ ከምሴና ባቲ ከተማ የተመረጡ ናቸው ያሉት በደሴና አካባቢው የአልማ -ዩኤስ አይድ ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪ መከላከል፤ እንክብካቤና ህክምና ፕሮጀክት የኦቪሲ አገልግሎት ስፔሻሊስት አቶ መስፍን ሰሎሞን ናቸው፡፡
Read Moreጃፓን ሀገር የሚገኘው አደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበር ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ያሰባሰበውን 608 ሺ የጀፓን የን ወይም 249 ሺ 355 የኢትዮጲያ ብር የሚገመት በአሸባሪው ትህነግ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኞች የሚውል ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ድጋፉ ከሰሜን ወሎ ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ጦሳ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተጠልለው ለሚገኙ በቁጥር 450 እማዎራዎችና ህፃናት እንዲሰጥ ለጋሾች በጠየቁት መሰረት 850 ሊትር ዘይት እና 42.5 ኩንታል ሩዝ ግዥ ተፈፅሞ በአማራ ልማት ማህበር በኩል በእለቱ ርክክብ ተደርጎ ለተፈናቀሉ ዜጎች ተሰራጭቷል፡፡ ድጋፉ የድረሳቸው አስተያየት ሰጭዎች እንደገለፁት አማራ ልማት ማህበር ጃፓን ሀገር የሚገኘውን አደይ አበባ ኢትዮጲያ ማህበርን በማስተባበር ያደረገው ድጋፍ እጅግ ጠቃሚና በክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ነው ብለዋል፡፡ በአማራ ልማት ማህበር...
Read Moreአማራ ልማት ማህበር-ዩ ኤስ ኤድ አፈፃፀም የኤች አይቪ ኤድስ ችግሮችን በመፍታትና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተሻለ ክልል መፍጠር እንደሚቻል ያሳየ ነው ሲሉ የፕሮጀክቱ ቁልፍ የባለድርሻ አካላት ገለፁ፡፡ አልማ -ዩኤስ ኤድ ፕሮጀክት የአንድ አመት ጉዞ አፈፃፀም ላይ ለመምከር በዳንግላ ከተማ በጠራው መድረክ የተሳተፉ የክልሉ የጤና፤የኢኮኖሚ ትብብር፤የፕሮጀክቱ ፈፃሚ ባለድርሻ አካላት እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ቆይታው በክልሉ 33 ወረዳዎችና ሁሉም ዞኖች የኤች አይቪ/ኤድስ መከላከል፤እንክብካቤና ህክምና ስራ ላይ የሴክተሩን ክፍተት በመሙላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡ በጤና ቢሮ የኤች አይቪ አይድስ ምርመራ ቡድን አስተባባሪ አቶ ሰዒድ ፈንቴ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ከ9-14 አመት ዕድሜ በሚገኙ ወላጅ አልባ ህፃናት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ ዘላቂ ው...
Read Moreየአማራ ልማት ማህበር ህውሃት በከፈተው ጦርነት በሰሜን ጎንደር ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሚሆን የፊኖ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል። ማህበሩ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚውል 230 ኩንታል የፊኖ ዱቄት በደባርቅ ከተማ በመገኘት ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል። የአልማ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ÷ማህበሩ ከአሁን ቀደም በክልሉ ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በመተከል፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች የተለያዩ ድጋፎች ማድረጉን አስታውሰዋል። አሁንም በሰሜን ጎንደር ዞን በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ዜጎችን ችግር ለመጋራት በማሰብ ግምቱ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 230 ኩንታል የፊኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገበ አንዱዓለም በበኩላቸው÷ የተ...
Read MoreBahir Dar: 3, September, 2021(AMC)-Amhara Development Association announced that it will focus on capacity building and rehabilitation of displaced people alongside sustainable development in 2021/22. Melaku Fenta, CEO of the association, said the strategic transformation plan of the association has been implemented in a number of challenging situations. According to Melaku, one of the association's main activities for 2021/22 fiscal year is to recruit members, mobilize resources and strengt...
Read More