The News

አማራ ልማት ማህበር የምስራቅ ጎጃም አልማ ማስተባበሪያ በለውጥ ዕቅዱ ካስመረቃቸው ፕሮጀክቶች በከፊል

Posted on : July: 26/2022

አማራ ልማት ማህበር የምስራቅ ጎጃም አልማ ማስተባበሪያ በለውጥ ዕቅዱ ካስመረቃቸው ፕሮጀክቶች በከፊል

Read More

አማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በሰሜን ወሎ ዞን ሃራ ከተማ ከ13 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመረቀ።

Posted on : July: 26/2022

አማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በሰሜን ወሎ ዞን ሃራ ከተማ ከ13 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመረቀ።

Read More

የመፈፀም አቅሙ እያደገና የተቋም ግንባታ ተምሳሌት እየሆነ የመጣ የልማት ማህበር ነው ሲሉ የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ገለፁ ፡፡

Posted on : July: 07/2022

ክቡር አቶ መላኩ ፈንታ የልማት ማህበሩ 30ኛ አመት የምስረታ በዓል ዝግጅት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የህዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት በጥቂት በጎ-ፈቃደኞች የተቋቋመው አልማ ሶስት አስርታትን አስቆጥሮ በአሁኑ ሰዓት የሚሊዮኖች ተቋም፣ በየደረጃው የሚገኘውን ህብረተሰብ የሚያሳትፍ፣ ዓለማቀፍ ረጅ ድርጅቶች ሳይቀር በዋና ፈፃሚነት በጋር ለመስራት የሚመርጡት፤ በድምር ውጤት አላማውን እያሳካ እዚህ የደረሰ ፣የመፈፀም አቅሙ እያደገና የተቋም ግንባታ ተምሳሌት እየሆነ የመጣ ተቋም ሆኗል ብለዋል፡፡ የልማት ማህበሩ መቋቋም ወሳኝና አሳማኝ ነበር ያሉት ክቡር አቶ መላኩ በቦርድ አደረጃጀት በህዝብ ተጠሪ ተቋማትና ሲቪክ አደረጃጀቶች እንዲወከል ከማድረግ ጀምሮ ኢትዮጲያዊያንና ትቀውልደ ኢትዮጲያዊያን ከጥርጣሬ ወጥተው ከማህበሩ ጋር በመቀራረብ የጋራ ፕሮጀክት እየፈፀሙበት የሚገኝ አሳታፊ የህዝብ...

Read More

የአማራ ልማት ማህበር ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለውጤታማ የፕሮጀክት አፈፃፀምና የክልሉን ህዝብ ህይወት ለማሻሻል በምንችልበት የተሻለ አጋጣሚ ላይ ነን ሲሉ የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ገለፁ፡

Posted on : April: 21/2022

ክቡር አቶ መላኩ ፈንታ ይህን የገለፁት የልማት ማህበሩ የቢዝነስ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ በቅርቡ በአምስት አስተዳደር ዞኖች የአዋጭነት ጥናትና ዲዛይን ስራቸውን አጠናቆ ግንባታ ለማስጀመር ያዘጋጃቸውን የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች በክልሉ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተሰማርተው ለሚንቀሳቀሱ ከ10 በላይ የመንግስት ልማት ድርጅቶች በባህርዳርነ ባስተዋወቀበት መድረክ ላይ ነው፡፡ አልማ ከልዩ ልዩ አባላትና አጋር ድርጅቶች ከሚያገኘው የልማት ሀብት በተጨማሪ ከፌደራል ሲቪክ ተቋማት ኤጀንሲ በተሰጠው ፈቃድ መሰረት የራሱን የገቢ ማስገኛ ተቋማት አቋቁሞ እንደ አንድ የልማት ሀብት ምንጭ መጠቀምና ርዕዩን ለማሳካት በመትጋት ላይ መሆኑን የተናገሩት ክቡር አቶ መላኩ ፤ አልማ በደብረ ማርቆስ፤ ፍኖተ-ሰላም፤ ጎንደር ፤ ደብረ ታቦርና ወልድያ ከተሞች ባለ 10 ፎቅ ሁለገብ ህንፃ ፤ የዋንዛየ...

Read More

በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ ለደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጦርነት ተጎጅ ወገኖች 2 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር ወጭ የተደረገበት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

Posted on : February: 25/2022

በኢትዮጲያ ኦርተዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዋሽንግተን፤ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስና የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁ አቡነ አትናቲዎሰ ድጋፉን ለደቡብ ወሎ ና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊዎች ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት በጎ አድራጊ ወገኖቻችን ሀብት አሰባስቦ ከመላክ ባለፈ የጉደቱን መጠን በቦታው ተገኝተው በአይናቸው ማየትና መረዳት የሚችሉ ተወካይ መላካቸው ችግሩን ለመቅረፍና በትብብር ለመስራት ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡ በዋሽንግተን፤ ኦሪገን አይዳሆ እና አካባቢው፤ ሰበካ ጉባኤ የሚኖሩ ምዕመናን፤ ካህናትና ሊቃውንት በቀጣይ ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው የጠቀሱት ብፁ አቡነ ማርቆስ የስርጭት ፍትሀዊነትና ታማኒነት እንዲኖረው የየዞኑ ሀገረ-ስብከት ከ...

Read More