በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አበጀ ሙላት ይህን የገለፁት የወረዳውን የ2013 ዕቅድ አፈፃፀምና በ2014 በጀት አመት ዕቅድ እንዲሁም በአልማ የሚሰሩ ተግባራትን ገምግሞ ባፀደቀበት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው። የአማራ ልማት ማህበር የቡሬ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ትዕዛዙ አማራ ልማት ማህበረ ከምስረታው ጀምሮ ልዩ ለዩ ስትራተጅያዊ ዕቅዶችን በማዘጋጀት መንግስትን፤ ህዝቡንና አጋር ድርጅቶችን አቅም በማስተባበር የትምህርት ፣ ጤና እና በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ያልተቆጠበ ድገፍ በማድረግ ለይ የሚገኝ አገር በቀል የልማት ማህበር ነው። መንግስት ህብረተሰቡና አልማ ተቀናጅተው በ2013 ዓ.ም በዙሪያ ወረዳ ከደረጃ በታች የሆኑ አጠቃላይ ትምህርት ቤቶችን ገፅታ ደረጃ ለማስጠበቅ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ያወሱት...
Read Moreዶ/ር ማተቤ ተፈራ የአማራ ልማት ማህበር አባል ያልሆነ አማራ የምን አባል ሊሆን ይችላል ? ሲሉ ያጠየቁት ከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር የሚገኙ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች የ2013 ዓ.ም አፈፃፀምና 2014 ዓ.ም ዕቅድን ለማፅደቅ በባህር ዳር ከተማ ባካሄዱበት የምክክር መድረክ ሲያጠቃልሉ ነው፡፡ የማህበሩ ስራ አመራር ቦርድና የትምህርት ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ማተቤ ታፈረ አማራ ልማት ማህበር ከለውጥ ዕቅድ በፊት ባሉት አስር አመታት የተጓዘበትን የልማት ሀብት አሰባሰብ በሁለት የስትራተጅያዊ አመታት ብቻ ማንቀሳቀስ መቻሉ ክልላችን ውስጥ ለዘላቂ ልማትና ሀገራዊ ብልፅግናች መሰረት የሚሆን ያልተጠቀምንበት በርካታ አቅም መኖሩን አመላካች ነው ብለዋል፡፡ ልማት ማህበራችን እያከናወነ የሚገኘውን ዘላቂ ልማት ለሁሉም ባለድርሸ አካላት ማስገንዘብና ልማትን በሚደግፍ...
Read Moreከክልል እስከ ቀበሌ መዋቅር የሚገኙ የአማራ ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች ማህበሩ በባህር ዳር ከተማ ባዘጋጀው የ2013 ዓ.ም አፈፃፀምና 2014 ዓ.ም ዕቅድ ምክክር መድረክ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት በሁለት አመት የስትራተጅያዊ የለውጥ ዕቅዱ ቁልፍ ችግር ተብለው በተለዩት የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል ላይ ያሳየው ዕምርታ እጅግ ጠቃሚ እንደነበር አውስተው ዘርፉ ለክልላችን ዕድገትና ዘላቂ ልማት ወሳኝ የመሆኑን ያህል የአባላትን ህዝባዊ መሰረት በማስፋትና የማስፈፀም አቅም ውስንነት ታይቷል ብለዋል፡፡ ክፍተቱን በቀጣይ ለማሻሻል ልማት ማህበሩ በ2014 ዓ.ም ያፀቀደውን የዘላቂ ልማትና በአሸባሪው ትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ የማቋቋም ተግባር በሙሉ አቅም መደገፍ የሚያስችል የልማት ሀብት ለማንቀሳቀስ የማህበሩን ህዝባዊ መሰረት የማስፋት ስራ ላይ ትኩረ...
Read Moreዘጠኝ አባላት ያሉትና በአሜሪካ ፤አውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ የማህበሩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስተባባሪዎች ሰሞኑን በአዲስ አበባ የአልማ ጽ/ቤት ስራ ሃላፊዎች ጋር ባካሄዱት የውይይት መድረክ ላይ እንደገለፁት ህዝባዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት አልማ 2012-2014 በሚል መሪ ቃል ቀይሶ መንቀሳቀስ ከጀመረ ወዲህ ዳያስፖራው ማህበረሰብ ራሱን አደራጅቶ ከስትራቴጂክ እቅዱ ጋር በተጣጣመ መልኩ በክልሉ የሚታየውን የትምህር ቤቶች የጥራት ደረጃ ካለበት 16 ፐርሰንት ወደ 50 ፐርሰንት ከፍ ለማድረግ ያከናወናቸውን አስተዋፅዎች በዝርዝር ጠቅሰዋል፡፡ የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በሰ/አሜሪካና በእንግሊዝ ባደረጋቸው የመስክ ጉብኝቶችና ውይይቶች ወቅት ዳያስፖራው በክልሉ የሚታዩ ማህበራዊ ልማት ክፍተቶቸን ለመደገፍ ያሳየውን ፍላጎት ተከትሎ ከማህ...
Read Moreየአልማ ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ አበባው ታደሰ እንደገለፁት 308 ሺ ብር ወጭ የተደረገበትንና መስከረም 12/2014 ዓ.ም የአንድ ሴሚሰተር ደብተርና እስክርፒቶ የተደገፉት አንድ ሺ አንድ መቶ ሶስት ህፃናት ተማሪዎችም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን ፕሮጀክቱ አረጋግጧል ብለዋል፡፡ የድጋፉ ተጠቃሚዎች በደሴ፤ ቃሉ፤ ከምሴና ባቲ ከተማ የተመረጡ ናቸው ያሉት በደሴና አካባቢው የአልማ -ዩኤስ አይድ ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪ መከላከል፤ እንክብካቤና ህክምና ፕሮጀክት የኦቪሲ አገልግሎት ስፔሻሊስት አቶ መስፍን ሰሎሞን ናቸው፡፡
Read More