The News

የአማራ ልማት ማህበር በክልሉ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የምግብና የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

Posted on : October: 28/2020

ልማት ማህበሩ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚሰጠውን 12 ሺ 500 ባለ 50 ሉክ ደብተር፤12 ሺ 500 እስክርፒቶና 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄት በዙኑ ለተቋቋመው የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ ሀይል ዛሬ አስረክቧል፡፡ በብሄረሰብ ዞኑ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ -ሀይል አባልና የምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ መሀመድ ይማም በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት የአንበጣ መንጋው በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው የአማራ ልማት ማህበር ከተጎጅው ህብረተሰባችን ጎን ቆሞ አደጋውን ለመቆቋም የሰጠው ፈጣን ምላሽ ከዞኑ ህዝብ ልብ ዘንድ ከፍተኛ ቦታ አለው ብለዋል፡፡ የአማራ ልማት ማህበር ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ አቶ አበባው ታደሰ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት በበኩላቸው አልማ በዘላቂነት የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ ራዕይ ቀርፆ ከመንቀሳቀስ ባሻገር...

Read More

አማራ ልማት ማህበር ለማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ ምላሽ መስጠቱ በራስ የመተማመን ስሜት ፈጥሮልናል ሲሉ በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡

Posted on : October: 28/2020

ነዋሪወቹ ይህን የገለፁት ማህበሩ ሰብላቸው በአንበጣ ለወደመባቸው ቤተሰቦች ሚሰጥ 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄትና 10 ሺ 743 ባለ50 ሉክ ደብተርና 10 ሺ እስክርቢቶ ቦታው ድረስ በመሄድ ባስረከበበት ወቅት ነው፡፡ ማህበሩ ድጋፉን ለህብረተሰቡ ባስረከበበት ወቅት የወረባቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሊድ መሀመድ እንዳብራሩት አልማ ህዝባዊ ተሰትፎ ለዘላቂ ልማት 2012-2014 በሚል መሪ ቃል የወረዳውን ትምህርት ቤቶች ደረጃ በማሻሻል በሚገኝበት ወቅት ይህ አይነቱ አደጋ በአካባቢያቸው ሲፈጠር ደግሞ ህብረተሰቡን ለመደገፍ ፈጥኖ ያቀረበው አልማ ምህብና የትምህርት ቁሳቁስ በማህበራችን ላይ መተማመን ስሜት ፈጥሮብኛል ብለዋል፡፡ አርሶ አደሩ ምርቱን ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦናም በተጎዳበት ወቅት አማራ ልማት ማህበር ያቀረበው ድጋፍ ለችግር ደራሽነቱን ብቻ ሳይሆን ወገንተኛነቱንም በተግባር ያሳየበት...

Read More

መመረቅ እንጅ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ልማዳችን አይሆንም! ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአብክመ ርዕሰ-መስተዳደር

Posted on : October: 23/2020

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ይህን ያሉት ጥቅምት 8/2013 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ አልማ በ12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን የገጠር ፋና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው ፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ርዕሰ -መስተዳድሩ በምረቃው ወቅት ባስተላለፍት መልዕክት አማራ ልማት ማህበር በጎዛምን ወረዳ አዲስና ጉሊት ቀበሌ የገጠር ፋና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ሲገነባ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ነው፡፡ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች አልማ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ፡፡ የዚህ ውጤት ደግሞ የህዝብ ተሳትፎ ነው ፡፡ ተሳትፎው ደግሞ በገንዘብ መዋጮ...

Read More

የአማራ ልማት ማህበር በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለተጎዳባቸው ሶስት ወረዳዎች የአልሚ ምግብና የትምህርት መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

Posted on : October: 23/2020

ልማት ማህበሩ በዞኑ ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለተጎዳባቸው ሀብሩ ራያ ቆቦና ጉባላፍቶ ወረዳዎ ነዋሪዎች የሚታደለውን 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄት፤ 10 ሺ 743 ባለ 50 ሉክ ደብተርና 10 ሺ 743 እስክርቢቶ ለዞኑ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ- ሀይል ዛሬ ያስረከበው ወልድያና አካባቢው በሚገኘው የአልማ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በመገኘት ነው፡፡ የዞኑ የአመንዝኮ ግብረ-ሀይል አባልና የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ይመር በርክክብ ስነስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት በዞኑ የአንበጣ መንጋ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ አደጋውን ለመቀልበስ የክልሉ መንግስትና የዞኑ ማህበረሰብ በርብርብ ላይ በሚገኝበት ወቅት አልማ ያቀረበልን ድጋፍ የማህበሩን ህዝባዊነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የዞኑ ትምህርት ምክትል መምሪያ ሀላፊና የአመንዝኮ ግብረ-ሀይል አባል የሆኑት አቶ ሰጠ ታደ...

Read More

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል አልማ ፍቱን መዳህኒት ነው!!

Posted on : October: 02/2020

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያደርስ የሚችለውን ተፅዕኖ በመቆቋም የተሳካ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከአማራ ልማት ማህበር ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊና የአማራ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ገለፁ፤፤ ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ ዛሬ ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በብሄራዊ ክልሉ ከ6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችን ተመዝግበው ጥቅምት ዘጠኛ 16 እና 30/2013 ዓ.ም መደበኛ ትምህርታቸውን ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ ከኮቪድ -19 ወረርሽኝን መከላከል በሚያስችል መንገድ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ክልላዊ ቅንጅትና ትብብር ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር ይልቃል ተማሪዎች ከተለመደው ውጭ ርቀታቸውን ጠብቀው በመቀመጣቸው ምክንያት በመማሪያ ክፍል በኩል...

Read More