The News

የመተማ ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ ።

Posted on : December: 16/2020

የመተማ ወረዳ የአማራ ልማት ማህበር ከመደበኛ አባላት በተሰበሰበ 1ሚሊዩን 500ሺ ብር በመተማ ወረዳ ዲቪኮ ቀበሌ የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 ብሎክ አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት አዲስ ህንጻ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን የመተማ ወረዳ አልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳለው ባዘዘው ገልጸዋል ። ኃላፊው አክለውም የዲቪኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ የተከፈተ እና በ2012 ዓ.ም እንዲጀምር የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በፈቀደው መሰረት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ አማራ ልማት ማህበር በስታንዳርዱ መሰረት ግንባታውን ገንብቶ ማጠናቀቁን እና ለምረቃ ዝግጁ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ፡፡

Read More

አማራ ልማት ማህበር የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚያገለግል የመዋኛና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት መ/ቤት አስረከበ ፡፡

Posted on : December: 15/2020

ድጋፉን ለጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት መ/ቤት ርክክብ ያደረጉት የአልማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መዝገበ አንዷለም የቁሳቁስ ድጋፉ በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን እንቦጭ ለመከላከል የሚያገለግል 300 የዋና ልብስ ፤500 የእጅ ጓንት 56 ካርቶን የገላ ሳሙና በድምሩ 700 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚያገለግለው ቁሳቁስ የተገኘው የአልማ በጎ ፈቃደኞችንና ዳያስፖራውን የተቀናጀ አቅም ወደ ልማት የማስገባትና ክልሉን የመደገፍ ፍላጎት ያላቸውን አካላት በማስተባበር ሂደት በአሜሪካ የዲሲ ፤ሜሪላንድና ቨርጅንያ የማህበሩ አባላት መሆናቸውን አቶ መዝገበ ተናግረዋል፡፡ የጣና ሀይቅና ሌሎች የውሀ አካላት ጥበቃና ልማት ተወካይ አቶ ጤናው ምንውየለት የቁሳቁስ ድጋፉን ሲረከቡ እንደገለፁት አልማ በትምህርት ጤናና ስራ እድ...

Read More

የአማራ ልማት ማህበር በክልሉ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የምግብና የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

Posted on : October: 28/2020

ልማት ማህበሩ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚሰጠውን 12 ሺ 500 ባለ 50 ሉክ ደብተር፤12 ሺ 500 እስክርፒቶና 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄት በዙኑ ለተቋቋመው የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ ሀይል ዛሬ አስረክቧል፡፡ በብሄረሰብ ዞኑ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ግብረ -ሀይል አባልና የምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ መሀመድ ይማም በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት የአንበጣ መንጋው በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው የአማራ ልማት ማህበር ከተጎጅው ህብረተሰባችን ጎን ቆሞ አደጋውን ለመቆቋም የሰጠው ፈጣን ምላሽ ከዞኑ ህዝብ ልብ ዘንድ ከፍተኛ ቦታ አለው ብለዋል፡፡ የአማራ ልማት ማህበር ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ አቶ አበባው ታደሰ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት በበኩላቸው አልማ በዘላቂነት የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግር ለመቅረፍ ራዕይ ቀርፆ ከመንቀሳቀስ ባሻገር...

Read More

አማራ ልማት ማህበር ለማህበራዊ ልማት ጎን ለጎን በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ ምላሽ መስጠቱ በራስ የመተማመን ስሜት ፈጥሮልናል ሲሉ በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡

Posted on : October: 28/2020

ነዋሪወቹ ይህን የገለፁት ማህበሩ ሰብላቸው በአንበጣ ለወደመባቸው ቤተሰቦች ሚሰጥ 200 ኩንታል የፊኖ ዱቄትና 10 ሺ 743 ባለ50 ሉክ ደብተርና 10 ሺ እስክርቢቶ ቦታው ድረስ በመሄድ ባስረከበበት ወቅት ነው፡፡ ማህበሩ ድጋፉን ለህብረተሰቡ ባስረከበበት ወቅት የወረባቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሊድ መሀመድ እንዳብራሩት አልማ ህዝባዊ ተሰትፎ ለዘላቂ ልማት 2012-2014 በሚል መሪ ቃል የወረዳውን ትምህርት ቤቶች ደረጃ በማሻሻል በሚገኝበት ወቅት ይህ አይነቱ አደጋ በአካባቢያቸው ሲፈጠር ደግሞ ህብረተሰቡን ለመደገፍ ፈጥኖ ያቀረበው አልማ ምህብና የትምህርት ቁሳቁስ በማህበራችን ላይ መተማመን ስሜት ፈጥሮብኛል ብለዋል፡፡ አርሶ አደሩ ምርቱን ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦናም በተጎዳበት ወቅት አማራ ልማት ማህበር ያቀረበው ድጋፍ ለችግር ደራሽነቱን ብቻ ሳይሆን ወገንተኛነቱንም በተግባር ያሳየበት...

Read More

መመረቅ እንጅ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ልማዳችን አይሆንም! ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአብክመ ርዕሰ-መስተዳደር

Posted on : October: 23/2020

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ይህን ያሉት ጥቅምት 8/2013 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ አልማ በ12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን የገጠር ፋና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው ፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ርዕሰ -መስተዳድሩ በምረቃው ወቅት ባስተላለፍት መልዕክት አማራ ልማት ማህበር በጎዛምን ወረዳ አዲስና ጉሊት ቀበሌ የገጠር ፋና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ሲገነባ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ነው፡፡ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች አልማ ሰፊ ስራ እየተሰራ ነው ፡፡ የዚህ ውጤት ደግሞ የህዝብ ተሳትፎ ነው ፡፡ ተሳትፎው ደግሞ በገንዘብ መዋጮ...

Read More